ካህኑ ሳዶቅም ከተቀደሰው ድንኳን ይዞት የመጣውን የቅባት ዘይት መያዣ ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን ቀባው፤ በዚህን ጊዜ እምቢልታ ነፉ፤ ሕዝቡም ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ረጅም ዕድሜ ለንጉሥ ሰሎሞን!” አሉ፤
ዘፀአት 30:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ምርጥ የሆኑ ቅመሞችን፥ ስድስት ኪሎ ግራም ፈሳሽ ከርቤ፥ ሦስት ኪሎ ግራም ጣፋጭ ሽታ ያለውን ቀረፋ፥ ሦስት ኪሎ ግራም ጣፋጭ ሽታ ያለውን የጠጅ ሣርና፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ምርጥ ቅመሞችን፣ ዐምስት መቶ ሰቅል ፈሳሽ ከርቤ፣ ግማሽ ይኸውም ሁለት መቶ ዐምሳ ሰቅል ጣፋጭ ቀረፋ፣ ሁለት መቶ ዐምሳ ሰቅል ከሙን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ምርጥ የሆኑትን ቅመሞች ለራስህ ውሰድ፤ ፈሳሽ ከርቤ አምስት መቶ ሰቅል፥ ግማሽ ይኸውም ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል የቀረፋ ቅመም፥ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንተም ክቡሩን ሽቱ ውሰድ፤ የተመረጠ የከርቤ አበባ አምስት መቶ ሰቅል፥ የዚህም ግማሽ ጣፋጭ ቀረፋ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፤ ያማረ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም ክቡሩን ሽቱ ውሰድ፤ የተመረጠ ከርቤ አምስት መቶ ሰቅል፥ ግማሽም ጣፋጭ ቀረፋ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥ |
ካህኑ ሳዶቅም ከተቀደሰው ድንኳን ይዞት የመጣውን የቅባት ዘይት መያዣ ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን ቀባው፤ በዚህን ጊዜ እምቢልታ ነፉ፤ ሕዝቡም ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ረጅም ዕድሜ ለንጉሥ ሰሎሞን!” አሉ፤
ከእነርሱም አንዳዶች ደግሞ ለሌሎቹ ንዋያተ ቅድሳት፥ ለዱቄቱ፥ ለወይን ጠጁ፥ ለወይራ ዘይቱ፥ ለዕጣንና ለልዩ ልዩ ቅመማቅመም ሁሉ ኀላፊዎች ነበሩ፤
ከከርቤ፥ ከእሬትና ከብርጒድ የተቀመመ ሽቶ በንጉሣዊ ልብስህ ላይ ተርከፍክፎአል፤ በዝሆን ጥርስ በተጌጠው ቤተ መንግሥትህም የበገና ሙዚቃ ቃና ያስደስትሃል።
የቅባቱ ዘይትና ለተቀደሰው ስፍራ የሚሆነው መዓዛው ጣፋጭ የሆነ ዕጣን፤ ልክ እኔ አንተን ባዘዝኩት ዐይነት እነዚህን ሁሉ ነገሮች ይሠራሉ።”
ናርዶስ፥ ቀጋ፥ ጠጅ ሣርና ቀረፋ፥ እንዲሁም ሽታቸው እንደ ዕጣን መዓዛ ያላቸው ልዩ ልዩ ተክሎች ይገኙባታል፤ እንዲሁም ከርቤ፥ የሬት አበባና ልዩ ልዩ የቅመማቅመም ተክሎች ይበቅሉባታል።
በገንዘባችሁ መልካም መዓዛ ያለው ዕጣን አልገዛችሁልኝም፤ ወይም በስብ መሥዋዕታችሁ አላረካችሁኝም፤ ነገር ግን በኃጢአታችሁ ብዛት ሸክም ሆናችሁብኝ። በበደላችሁም ብዛት አሰለቻችሁኝ።
ከሳባ የሚያመጡልኝ ዕጣን፥ ከሩቅ አገሮች የሚያመጡልኝ ቅመማቅመም ሁሉ ለእኔ ምን ይረባኛል? መባቸውን አልቀበለውም፤ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘኝም።
በኡዛል የሚኖሩ ዳናውያንና ግሪኮች አሞናውያን ያንቺን ዕቃዎች ለመግዛት የንግድ ስምምነት አደረጉ፤ እነርሱም በአንቺ ሸቀጦች ልዋጭ ቀልጦ የተሠራ ብረት፥ ቅመማ ቅመምና የጠጅ ሣር አቀረቡ።
“የካህኑም የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት፥ ጣፋጭ ሽታ ባለው ዕጣን፥ ዘወትር በሚቀርበው በእህሉ ቊርባንና በቅባቱ ዘይት ላይ ኀላፊነት ይኖረዋል፤ እንዲሁም የመገናኛው ድንኳን በሙሉ፥ በእርሱም ውስጥ ያለውን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕቃ ሁሉ ይጠብቃል።”
ሳሙኤል የወይራ ዘይት መያዣውን ቀንድ ወስዶ በሳኦል ራስ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም። ከዚያም በኋላ “እግዚአብሔር በሕዝቡ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን ቀባህ፤ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ነግሠህ በዙሪያቸው ካሉ ጠላቶች ታድናቸዋለህ እግዚአብሔር በርስቱ ላይ የሾመህ ለመሆኑ ይህ ማስረጃ ነው፤