ዘፀአት 30:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤልን ሕዝብ በምትቈጥርበት ጊዜ በሕዝብ ቈጠራው ወቅት መቅሠፍት እንዳይደርስባቸው እያንዳንዱ ሰው ለሕይወቱ ቤዛ የሚሆን ዋጋ ይክፈል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእስራኤላውያንን ጠቅላላ ቈጠራ በምታደርግበት ጊዜ እያንዳንዱ ሰው በሚቈጠርበት ወቅት ለሕይወቱ ቤዛ የሚሆን ወጆ ለእግዚአብሔር መክፈል አለበት፤ በዚህም ዐይነት ስትቈጥራቸው በእነርሱ ላይ መቅሠፍት አይመጣም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንተ የእስራኤልን ልጆች ቍጥር ተቀብለህ በቆጠርሃቸው ጊዜ መቅሰፍት እንዳይሆንባቸው፥ በቆጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቁጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንተ የእስራኤልን ልጆች ቍጥር የወሰድህ እንደ ሆነ በቈጠርሃቸው ጊዜ መቅሠፍት እንዳይሆንባቸው፥ በቈጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ የእስራኤልን ልጆች ቍጥር ተቀብለህ፥ በቆጠርሃቸው ጊዜ መቅሰፍት እንዳይሆንባቸው፥ በቆጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ። |
“በምድርህ ላይ ሦስት ዓመት ራብ ከሚሆን ወይም ሦስት ወር ጠላቶችህ ከሚያሳድዱህ ወይም እግዚአብሔር በምድርህ ላይ ለሦስት ቀን በሰይፍ ከሚመታህና ቸነፈር በምድሪቱ ላይ አምጥቶ በእስራኤል ምድር ሁሉ በሞት የሚቀሥፍ መልአክ ከሚልክብህ የትኛውን ትመርጣለህ? እንግዲህ ወደ እግዚአብሔር የማቀርበውን መልስ ስጠኝ።”
ኢዮአብም “ንጉሥ ሆይ፥ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ አሁን ካሉት ይልቅ በመቶ እጅ ያብዛልህ! እነርሱ በሙሉ የአንተ አገልጋዮች ናቸው፤ ታዲያ አንተ የሕዝብ ቈጠራ በማድረግ ሕዝቡን በሙሉ በደለኛ ለምን ታደርጋለህ?” አለ።
የጸሩያ ልጅ ኢዮአብ የሕዝብ ቈጠራ ማድረግ ጀምሮ ሳይጨርስ ቀርቶ ነበር፤ በዚህ በሕዝብ ቈጠራ ምክንያት እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ቀጥቶ ስለ ነበር የመጨረሻው ቊጥር በንጉሥ ዳዊት መንግሥት የታሪክ መዝገብ ውስጥ አልተመዘገበም ነበር።
ስለዚህ ንጉሥ ኢዮአስ የሌዋውያኑን መሪ ዮዳሄን ጠርቶ፦ “የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ፥ እግዚአብሔር ለሚመለክበት ድንኳን አገልግሎት የሚሆን ግብር የእስራኤል ሕዝብ እንዲያዋጣ ያዘዘውን ሌዋውያኑ ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ሕዝብ ሰብስበው ያመጡ ዘንድ ስለምን አላተጋሃቸውም?” አለ።
ከዚህ በኋላ ሌዋውያኑ በመላው ኢየሩሳሌምና በይሁዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ሁሉ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእስራኤል ሕዝብ እንዲሰበሰብ ያዘዘውን ግብር ለእግዚአብሔር እንዲያመጡ ትእዛዝ አስተላለፉ፤
ስለዚህ እያንዳንዳችን ያገኘነውን የወርቅ ጌጣጌጥ ማለትም የእግር አልቦውን፥ የእጅ አንባሩን፥ የጣት ቀለበቱን፥ የጆሮ ጒትቻውንና የአንገት ድሪውን ሁሉ ለኃጢአታችን ማስተስረያ ለእግዚአብሔር ቊርባን ይሆን ዘንድ ይዘን መጥተናል።”
ሰዎችን ሁሉ ከኃጢአት ለመዋጀት ራሱን ቤዛ አድርጎ የሰጠ እርሱ ነው፤ ይህም ትክክለኛው ጊዜ ሲደርስ የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ የሚያስረዳ ምስክርነት ነው።