ለአደባባዩ በር ርዝመታቸው ዘጠኝ ሜትር የሆነ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ የተሠራ በጥልፍ ያጌጠ መጋረጃ ይኑረው፤ የሚደግፉትም አራት እግሮች ያሉአቸው አራት ምሰሶዎች ይኑሩት።
ዘፀአት 27:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ በብር ዘንጎች ይያያዙ፤ ኲላቦቻቸው ከብር፥ እግሮቻቸውም ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች፣ ኵላቦችና የንሓስ መቆሚያዎች ይኑሯቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአደባባዩም ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ በብር ይያያዙ፥ ኩላቦቻቸው ከብር እግሮቻቸው ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዙሪያውም ያሉ የአደባባዩ ምሰሶዎች ሁሉ በብር የተለበጡ ይሁኑ፤ የብርም ክባሶች፥ የናስም እግሮች ይሁኑላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአደባባዩም ዙሪያ ላሉት ምሰሶች ሁሉ የብር ዘንጎች፥ የብርም ኩላቦች፥ የናስም እግሮች ይሁኑላቸው። |
ለአደባባዩ በር ርዝመታቸው ዘጠኝ ሜትር የሆነ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ የተሠራ በጥልፍ ያጌጠ መጋረጃ ይኑረው፤ የሚደግፉትም አራት እግሮች ያሉአቸው አራት ምሰሶዎች ይኑሩት።
የድንኳኑ አደባባይ ርዝመቱ አርባ አራት ሜትር የጐኑ ስፋት ኻያ ሁለት ሜትር፥ ከፍታውም ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ይሁን፤ መጋረጃዎቹ ከጥሩ በፍታ የተሠሩ ሆነው የነሐስ እግሮች ይኑሩአቸው።
ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ የሆነው ደጃፍ የሚቆምባቸውን እግሮች፥ ከነሐስ መከላከያው ጋር የነሐስ መሠዊያውን፥ ለመሠዊያው መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ ከዚህ ነሐስ ሠራ፤