ዘፀአት 25:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመብራት የሚሆን የወይራ ዘይት፥ ለቅባት ዘይትና ለዕጣን ሽታ የሚሆን ቅመማ ቅመም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመብራት የወይራ ዘይት፤ ለቅብዐ ዘይቱና ለጣፋጭ መዐዛ ላለው ዕጣን የሚሆኑ ቅመሞች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመብራት የሚሆን ዘይት፥ ለቅባት የሚሆን ዘይትና ለጣፋጭ ዕጣን የሚሆን ቅመም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመብራትም ዘይት፥ ለቅብዐት ዘይትና ለጣፋጭ ዕጣን ቅመም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመብራትም ዘይት፥ ለቅብዓት ዘይትና ለጣፋጭ ዕጣን ቅመም፥ |
“የካህኑም የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት፥ ጣፋጭ ሽታ ባለው ዕጣን፥ ዘወትር በሚቀርበው በእህሉ ቊርባንና በቅባቱ ዘይት ላይ ኀላፊነት ይኖረዋል፤ እንዲሁም የመገናኛው ድንኳን በሙሉ፥ በእርሱም ውስጥ ያለውን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕቃ ሁሉ ይጠብቃል።”