ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ ንጹሕ ሰዎችን ለመጒዳት ጉቦ የማይቀበል፥ እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ከቶ አይናወጥም። በሰላም ይኖራል እንጂ ከቶ አይናወጥም።
ዘፀአት 23:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ትክክለኛ የሆነውን ነገር እንዳያዩ ዐይናቸውን ስለሚያሳውርና የንጹሕ ሰዎችንም ፍርድ ስለሚያጣምም ጉቦ አትቀበል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጕቦ አትቀበል፤ ጕቦ አጥርተው የሚያዩትን ሰዎች ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉቦን አትቀበል፤ ጉቦ የሚያዩ ሰዎችን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መማለጃን አትቀበል፤ መማለጃ የዐይናማዎችን ዐይን ያሳውራልና፥ እውነተኛ ቃልንም ያጣምማልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማማለጃን አትቀበል፤ ማማለጃ የዓይናማዎችን ሰዎች ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና። |
ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ ንጹሕ ሰዎችን ለመጒዳት ጉቦ የማይቀበል፥ እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ከቶ አይናወጥም። በሰላም ይኖራል እንጂ ከቶ አይናወጥም።
ይህን ዐይነት ከንቱ መባ ከእንግዲህ ወዲህ አታቅርቡ፤ የምታጥኑት ዕጣን በፊቴ አጸያፊ ነው፤ አዲስ ጨረቃ የምትወጣበት የወር መባቻችሁና ሰንበቶቻችሁ፥ መንፈሳዊ ስብሰባዎቻችሁም በኃጢአት የተበከሉ ስለ ሆኑ አልወደድሁላችሁም።
መሪዎችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ግብረ አበሮች ሆኑ፤ እያንዳንዱ ሁልጊዜ ገጸ በረከትና ጉቦ ይቀበላል፤ አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች መብት አይጠብቁም፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች አቤቱታ አይሰሙም።
በእውነትና በትክክል የሚናገሩ፥ በግፍ የሚገኝን ትርፍ የሚጸየፉ፥ ጉቦን ከመቀበል ይልቅ የሚያስወግዱ፥ ስለ ነፍስ ግድያ መስማት የማይፈልጉና፥ ክፉ ነገርን ከማየት ዐይኖቻቸውን የሚጨፍኑ፥
ከሕዝብሽ አንዳንዶቹ ገንዘብ ተቀብለው ሰው ይገድላሉ፤ አንዳንዶቹ ለገዛ ወገኖቻቸው ለእስራኤላውያን ሳይቀር በአራጣ ያበድራሉ፤ እነርሱንም በመበዝበዝ ያለ አግባብ ይበለጽጋሉ፤ እኔንም ፈጽሞ ረስተዋል፤” ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።
በደላችሁ ምን ያኽል እንደ በዛና ኃጢአታችሁም ምን ያኽል ከባድ እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤ ደጋግ ሰዎችን ታስጨንቃላችሁ፤ ጉቦ እየተቀበላችሁ በየፍርድ አደባባዩ የምስኪኖችን ፍትሕ ታጣምማላችሁ።
እጆቻቸው ክፉ ነገርን ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ባለ ሥልጣኑና ዳኛው ጉቦ ይጠይቃሉ፤ ኀይለኛ ፍላጎቱን በግዴታ ተግባራዊ ያስደርጋል፤ በዚህም ዐይነት ሁሉም ፍርድን ያጣምማሉ።
እግዚአብሔር አምላካችሁ ከባዕዳን አማልክት ሁሉና ከኀይላትም ሁሉ በላይ ታላቅና ብርቱ ስለ ሆነ በፍርሃት መከበር ይገባዋል። እርሱ በፍርድ አያዳላም፤ ጉቦም አይቀበልም።
እነሆ አሁን በፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ንጉሥ ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወስጄአለሁ? የማንንስ አህያ ወስጄአለሁ? ማንንስ አታልዬአለሁ? ማንንስ ጨቊኜአለሁ? ፍርድን ለማዛባት ከማን ላይ ጉቦ ተቀብዬአለሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን አድርጌ ከሆነ የወሰድኩትን ለመመለስ ዝግጁ ነኝ።”
ነገር ግን የአባታቸውን መልካም አርአያነት አልተከተሉም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ የገንዘብ ጥቅም ፈላጊዎች ሆነው ጉቦ እየተቀበሉ ፍርድን ያጣምሙ ነበር።