ከአባቴ ቤትና ከትውልድ አገሬ አውጥቶ ይህን ምድር ለዘሬ እንደሚሰጥ በመሐላ ቃል የገባልኝ እግዚአብሔር፥ የሰማይ አምላክ ከዚያ ለልጄ ሚስት ማግኘት እንድትችል መልአኩን በፊትህ ይልካል።
ዘፀአት 23:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልአኬም ፊት ፊትህ በመሄድ ወደ አሞራውያን፥ ሒታውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ከነዓናውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን ምድር ይወስድሃል፤ እኔም እነርሱን አጠፋቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልአኬ በፊትህ ይሄዳል፤ አንተንም ወደ አሞራውያን፣ ወደ ኬጢያውያን፣ ወደ ፌርዛውያን፣ ወደ ከነዓናውያን፣ ወደ ኤዊያውያንና ኢያቡሳውያን ምድር ያስገባሃል፤ እኔም እነርሱን አጠፋቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና፥ ወደ አሞራውያን፥ ወደ ኬጢያውያን፥ ወደ ፌርዛውያን፥ ወደ ከነዓናውያን፥ ወደ ኤዊያውያንና ወደ እያቡሳውያን ያገባሃል፤ እኔም አጠፋቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና፥ ወደ አሞሬዎናውያንም፥ ወደ ኬጤዎናውያንም፥ ወደ ፌርዜዎናውያንም፥ ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያንም፥ ወደ ኤዌዎናውያንም፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያንም ያገባሃል፤ እኔም አጠፋቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና፥ ወደ አሞራውያንም ወደ ኬጢያውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ከነዓናውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ እያቡሳውያንም ያገባሃል፤ እኔም አጠፋቸዋለሁ። |
ከአባቴ ቤትና ከትውልድ አገሬ አውጥቶ ይህን ምድር ለዘሬ እንደሚሰጥ በመሐላ ቃል የገባልኝ እግዚአብሔር፥ የሰማይ አምላክ ከዚያ ለልጄ ሚስት ማግኘት እንድትችል መልአኩን በፊትህ ይልካል።
ሙሴም እስራኤልን ለመታደግ እግዚአብሔር በግብጽ ንጉሥና በሕዝቡም ላይ ያደረገውን ድንቅ ነገር ሁሉ ለዐማቱ ተረከለት። እንዲሁም ሕዝቡ በመንገድ ላይ ሳሉ ምን ያኽል ብርቱ ፈተና እንደ ገጠማቸውና እግዚአብሔርም እንዴት እንዳዳናቸው ነገረው።
በግፍ ጭቈና ከሚሠቃዩባት ከግብጽ ምድር አውጥቼ እነሆ ዛሬ፥ ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን የሚኖሩባትን፥ በማርና በወተት የበለጸገች ሰፊና ለም የሆነች ምድር ልሰጣቸው ቃል ገብቻለሁ።
ነገር ግን እንደሚባላ እሳት የሆነ እግዚአብሔር አምላክህ በፊትህ የሚሄድ መሆኑን ዛሬ ታያለህ፤ አንተ ወደ ፊት በሄድህ መጠን እርሱ ድል ይነሣቸዋል፤ ስለዚህም እርሱ በሰጠው ተስፋ መሠረት እነርሱን ነቃቅለህ በማባረር በፍጥነት ታጠፋቸዋለህ።
ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ሰይፍ የያዘ አንድ ጐልማሳ በድንገት በፊቱ ቆሞ ታየው፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ “አንተ የእኛ ወገን ነህ ወይስ የጠላቶቻችን?” አለው።
ከዮርዳኖስ ማዶ በተራራማውና በቈላማው አገሮች፥ በሜዲቴራኒያን ባሕር ጠረፍ፥ እስከ ሊባኖስ ድረስ ያሉት የሒታውያን፥ የአሞራውያን፥ የከነዓናውያን፥ የፔሩዛውያን የኤዊያውያንና የኢያቡሳውያን ነገሥታት ይህን በሰሙ ጊዜ፥