ከዚህም ጋር በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የጢሮስ ተወላጆች ዓሣና ሌሎች ሸቀጦችን በየዐይነቱ በሰንበት ቀን ወደ ከተማይቱ እያስገቡ ለይሁዳ ሕዝብ ይሸጡ ነበር፤
ዘፀአት 23:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በሳምንት ስድስት ቀን ሥራህን ሁሉ ሥራ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ምንም ሥራ አትሥራበት፤ በዚህ ዐይነት አገልጋዮችህና ለአንተ የሚሠሩ መጻተኞች፥ እንዲሁም በሬህና አህያህ ዕረፍት አድርገው ይዋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ በሬህና አህያህ በቤትህ የተወለደው ባሪያና መጻተኛው ያርፉ ዘንድ በሰባተኛው ቀን ምንም አትሥራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ በሬህና አህያህ እንዲያርፉ የባርያህ ልጅና መጻተኛውም ዕረፍት እንዲሆንላቸው በሰባተኛው ቀን ዕረፍ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድስት ቀን ሥራህን ሁሉ ሥራ፤ በሬህና አህያህ ያርፉ ዘንድ ለባሪያህም ልጅ ለመጻተኛውም ዕረፍት ይሆን ዘንድ በሰባተኛው ቀን ዕረፍ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ በሬህና አህያህ ያርፉ ዘንድ ለባሪያህም ልጅ ለመጻተኛውም ዕረፍት ይሆን ዘንድ በሰባተኛው ቀን ዕረፍ። |
ከዚህም ጋር በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የጢሮስ ተወላጆች ዓሣና ሌሎች ሸቀጦችን በየዐይነቱ በሰንበት ቀን ወደ ከተማይቱ እያስገቡ ለይሁዳ ሕዝብ ይሸጡ ነበር፤
እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “የነገው ዕለት ለእርሱ ተለይቶ የተቀደሰ የዕረፍት ቀን እንዲሆን እግዚአብሔር አዞአል፤ ስለዚህ ዛሬውኑ የምትጋግሩትን ጋግሩ፤ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፤ የተረፈው ተከፍሎ ለነገ ይቀመጥ።”
በሰባተኛው ዓመት ግን በሕዝብህ መካከል የሚገኙ ድኾች ምግብ ያገኙ ዘንድ በምድሪቱ ላይ ምንም ነገር አታምርት፤ ምድሪቱ ታርፍ ዘንድ ተዋት፤ ከእነርሱ የተረፈውንም የምድር አራዊት ይመገቡት፤ የወይን ተክል ቦታህንና የወይራ ዘይት ዛፎችህንም እንደዚሁ አሳርፋቸው።
ሥራችሁን ሁሉ የምትሠሩባቸው ስድስት ቀኖች አሉላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ዕረፍት ታደርጉበት ዘንድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕለት ነው፤ በዚህ ቀን ሥራ የሚሠራበት ማንኛውም ሰው በሞት ይቀጣል፤
ሕዝቡም “እነሆ እኛ እንጾማለን፤ አንተ ግን አትመለከተንም፤ የማትመለከተንስ ከሆነ ሰውነታችንን ለምን እናዋርዳለን?” ይላሉ። እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “እነሆ እናንተ በምትጾሙበት ጊዜ የልባችሁን ፈቃድ ትፈጽማላችሁ፤ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ትጨቊናላችሁ፤
ሥራ የምትሠሩባቸው ስድስት ቀኖች አሉላችሁ፤ ሰባተኛው ዕለተ ሰንበት ግን የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ለአምልኮ ተሰብሰቡ እንጂ ምንም ሥራ አትሥሩበት፤ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ሰንበት ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕለት ነው፤
ኢየሱስ በሰንበት ቀን ስለ ፈወሰ የምኲራቡ አለቃ ተቈጣና ለሕዝቡ፦ “በሳምንት ውስጥ ሥራ የሚሠራባቸው ስድስት ቀኖች አሉ፤ በእነዚህ ቀኖች እየመጣችሁ ተፈወሱ፤ በሰንበት ቀን ግን አይሆንም” ብሎ ተናገረ።