ላደርገው የሚገባኝንም በልቤ ወስኜ የሕዝቡ መሪዎች የሆኑትን ባለሥልጣኖች “እናንተ እኮ የገዛ ወንድሞቻችሁን በመጨቈን አራጣ ታስከፍላላችሁ!” በማለት በቊጣ ገሠጽኳቸው። ለችግሩም መፍትሔ ለማግኘት ሕዝቡን በአንድነት ሰብስቤ
ዘፀአት 22:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእናንተም ላይ ተቈጥቼ በጦርነት እንድታልቁ አደርጋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ ባል አልባ፥ ልጆቻችሁም አባት አልባ ሆነው ይቀራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቍጣዬ ይነሣል፤ በሰይፍም እገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ መበለቶች፣ ልጆቻችሁም አባት የለሽ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአንተ ጋር ላለው ለአንዱ ድሃ ወገኔ ገንዘብ ብታበድረው፥ እንደ ባለ አራጣ አትሁንበት፥ ወለድም አታስከፍለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍጣዬም ይጸናባችኋል፤ በሰይፍም አስገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁም መበለቶች፥ ልጆቻችሁም ድሀ-አደጎች ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍጣዬም ይጸናባችኋል፥ በሰይፍም አስገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁም መበለት፥ ልጆቻችሁም ድሀ አደጎች ይሆናሉ። |
ላደርገው የሚገባኝንም በልቤ ወስኜ የሕዝቡ መሪዎች የሆኑትን ባለሥልጣኖች “እናንተ እኮ የገዛ ወንድሞቻችሁን በመጨቈን አራጣ ታስከፍላላችሁ!” በማለት በቊጣ ገሠጽኳቸው። ለችግሩም መፍትሔ ለማግኘት ሕዝቡን በአንድነት ሰብስቤ
ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ ንጹሕ ሰዎችን ለመጒዳት ጉቦ የማይቀበል፥ እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ከቶ አይናወጥም። በሰላም ይኖራል እንጂ ከቶ አይናወጥም።
በምድራችሁ ላይ የሚገኙት ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ብዛታቸው ከባሕር አሸዋ የሚበልጥ ሆኖአል፤ በእኩለ ቀን በወጣቶች እናቶች ላይ ሞትን አመጣለሁ በእነርሱም ላይ ሽብርንና ጭንቀትን በቅጽበት አመጣለሁ።
አምላክ ሆይ! አሁን ግን ልጆቻቸው በራብ እንዲያልቁ፥ እነርሱም በጦርነት እንዲወድቁ አድርግ፤ ሴቶቻቸው ያለ ባልና ያለ ልጅ ይቅሩ፤ ወንዶቻቸው በበሽታ ወጣቶቻቸውም በጦርነት ይደምሰሱ።
“በአቅራቢያህ የሚኖር እስራኤላዊ ወገንህ ደኽይቶ ራሱን መርዳት የማይችል ቢሆን በአጠገብህ መኖር ይችል ዘንድ ላስጠጋኸው መጻተኛ በምታደርገው ዐይነት የሚያስፈልገውን ሁሉ በፈቃድህ አድርግለት።
በእርሱ ኀይለኛ ቊጣ ፊት መቆም የሚችል ማን ነው? ቊጣውስ እንደ እሳት በነደደ ጊዜ የሚችለው ማነው? እንደ እሳት የሚያቃጥል ቊጣው በሚወርድበት ጊዜ አለቶች ተሰነጣጥቀው ይበታተናሉ።
ስጡ፤ ለእናንተም ይሰጣችኋል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ እንዲሁ ይሰፈርላችኋል፤ እንዲያውም በጥሩ መስፈሪያ ታምቆና ተጠቅጥቆ እስኪትረፈረፍ ድረስ ተሰፍሮ ይሰጣችኋል።”
ወለድ መጠየቅ የሚገባህ ከውጪ አገር ተወላጅ እንጂ ከእስራኤላዊ ወገንህ አይደለም፤ ይህን ሕግ ፈጽም፤ እግዚአብሔር አምላክህም ሄደህ በምትወርሳት ምድር የምትሠራውን ሁሉ ይባርክልሃል።
“ለእግዚአብሔር አምላክህ ስእለት በምታደርግበት ጊዜ ለመስጠት ወይም ለመፈጸም ቃል የገባህበትን ስእለት አታዘግይ፤ እግዚአብሔር አንተ የገባኸውን ቃል እንድትፈጽም ይፈልጋል፤ ስእለትህን ካልፈጸምክ ግን ኃጢአት ይሆንብሃል።