ዘፀአት 21:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሴትዮዋ ራስዋ ብርቱ ጒዳት የደረሰባት ከሆነች ቅጣቱ ‘በሕይወት ምትክ ሕይወት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን የከፋ ጕዳት ቢደርስ ሕይወት በሕይወት፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉዳት ቢደርስባት ግን ሕይወት ስለ ሕይወት፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተሥዕሎተ መልክእ የተፈጸመለት ፅንስ ቢያስወርዳት ግን ሕይወት በሕይወት፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጕዳት ግን ቢያገኛት ሕይወት በሕይወት፥ |
የሌላውን ሰው አጥንት ቢሰብር አጥንቱ ይሰበር፤ የሌላውን ሰው ዐይን ቢያወጣ ዐይኑ ይውጣ፤ ጥርስም ቢሰብር ጥርሱ ይሰበር። በሌላ ሰው ላይ ምንም ዐይነት ጒዳት ቢያደርስ የዚያው ዐይነት ጒዳት በእርሱ ላይ ይመለስበት።
በእንደዚህ ያለው ክፉ ነገር ላይ ሁሉ ምንም ዐይነት ምሕረት አይኑርህ፤ የቅጣቱም አፈጻጸም ሕይወት ያጠፋ፥ ሕይወቱ እንዲጠፋ፤ ዐይን ያጠፋ፥ ዐይኑ እንዲጠፋ፤ ጥርስ ያወለቀ፥ ጥርሱ እንዲወልቅ፤ እጅ የቈረጠ፥ እጁ እንዲቈረጥ፤ እግርም የሰበረ፥ እግሩ እንዲሰበር በማድረግ ይሁን።