ስለዚህም ቅጣቱ በኢዮአብና በቤተሰቡ ላይ ይውረድ! በዘመናት ሁሉ ከቤተሰቡ የአባለ ዘር ወይም የሥጋ ደዌ ያለበት ሰው አይጥፋ! እንዲሁም አካለ ስንኩል የሆነ ሰው፥ በጦር ሜዳ የሚሞት ወይም የሚበላው አጥቶ የሚራብ ሰው አይታጣ!”
ዘፀአት 21:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኋላም ተነሥቶ በትር እየተመረኰዘ መራመድ ቢቀጥል፤ ስለ ባከነበት ጊዜ የመታው ሰው ካሣ ይክፈለው፤ በደንብ እስከሚድንም ድረስ ተገቢውን እንክብካቤ ያድርግለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በትሩንም ይዞ ደጅ ለደጅ የሚል ቢሆን፣ በዱላ የመታው ሰው አይጠየቅበትም፤ ሆኖም ለተጐጂው ሰው ለባከነበት ጊዜ ገንዘብ ይክፈል፤ ፈጽሞ እስኪድን ክትትል ያድርግለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተነሥቶም በምርኩዝ ወደ ውጭ ቢወጣ፥ ሥራ ስላስፈታው ገንዘብ ከመክፈልና፥ እስኪፈወስም ድረስ ከማሳከም በቀር የመታው ሰው ከወንጀል ነጻ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተነሥቶም በምርኩዝ ወደ ሜዳ ቢወጣ፥ የመታው ንጹሕ ነው፤ ነገር ግን ተግባሩን ስላስፈታው ገንዘብ ይክፈለው፤ ለባለ መድኀኒትም ይክፈልለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተነሥቶም በምርኩዝ ወደ ሜዳ ቢወጣ፥ የመታው ንጹሕ ነው፤ ነገር ግን ተግባሩን ስላስፈታው ገንዘብ ይከፍለው ዘንድ፥ ያስፈውሰውም ዘንድ ግዴታ አለበት። |
ስለዚህም ቅጣቱ በኢዮአብና በቤተሰቡ ላይ ይውረድ! በዘመናት ሁሉ ከቤተሰቡ የአባለ ዘር ወይም የሥጋ ደዌ ያለበት ሰው አይጥፋ! እንዲሁም አካለ ስንኩል የሆነ ሰው፥ በጦር ሜዳ የሚሞት ወይም የሚበላው አጥቶ የሚራብ ሰው አይታጣ!”
“ሁለት ሰዎች ቢጣሉና አንደኛው ሌላውን በድንጋይ ቢፈነክተው ወይም በቡጢ ቢያቈስለው ካልገደለው በቀር በሞት አይቀጣ፤ የተመታው ሰው ታሞ በአልጋ ላይ ቢውል፥