የምድያም ነጋዴዎች የሆኑ እስማኤላውያን በዚያ በኩል ያልፉ ነበር፤ ስለዚህ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጒድጓድ ጐትተው በማውጣት ለእነዚህ እስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ወደ ግብጽ ይዘውት ሄዱ።
ዘፀአት 21:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሊሸጠው ወይም ባርያ አድርጎ ሊገዛው አስቦ ሰውን አፍኖ የሚወስድ ሁሉ በሞት ይቀጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንዱ ሌላውን ጠልፎ የሸጠ ወይም በተያዘ ጊዜ ከእጁ ላይ የተገኘበት ይገደል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውን ሰርቆ ቢሸጥ፥ ወይም በእጁ ቢገኝ፥ ፈጽሞ ይሙት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ በሞት ይቀጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውን ሰርቆ ቢሸጥ፥ ወይም በእጁ ቢገኝ፥ እርሱ ፈጽሞ ይገደል። |
የምድያም ነጋዴዎች የሆኑ እስማኤላውያን በዚያ በኩል ያልፉ ነበር፤ ስለዚህ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጒድጓድ ጐትተው በማውጣት ለእነዚህ እስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ወደ ግብጽ ይዘውት ሄዱ።
እኔ ከዕብራውያን አገር ወደዚህ የመጣሁት ወድጄ ሳይሆን ተሸጬ ነው፤ እዚህም አገር ከመጣሁ ወዲህ በእስር ቤት የምገኘው ምንም በደል ሳልፈጽም ነው።”
“እስራኤላዊ ወገኑን አፍኖ በመውሰድ ባሪያ አድርጎ የሚጠቀምበትና ወይም ለሌላ ሰው በባርነት አሳልፎ የሚሸጠው ማንም ሰው በሞት ይቀጣ፤ በዚህም ዐይነት ክፉ ነገርን ታስወግዳላችሁ።
ለአመንዝሮችና ግብረ ሰዶምን ለሚያደርጉ፥ ሰውን አፍነው በመውሰድ ለሚሸጡ ነጋዴዎችና ለውሸታሞች፥ በሐሰት ለሚምሉና የእውነተኛ ትምህርት ተቃራኒ የሆነውን ነገር ሁሉ ለሚያደርጉ ነው፤
በመርከባቸው የተጫነውም ወርቅ፥ ብር፥ የከበረ ድንጋይ፥ ዕንቊ፥ ቀጭን ልብስ፥ ሐምራዊ ልብስ፥ ሐር ልብስ፥ ቀይ ልብስና መልካም መዓዛ ያለው እንጨት ሁሉ፥ ከዝኆን ጥርስ፥ ውድ ከሆነ እንጨት፥ ከነሐስ፥ ከብረትና ከእብነበረድ የተሠራ ዕቃ ሁሉ፥