ዘፀአት 20:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ እኔ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባትህንና እናትህን አክብር፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፥ አባትህንና እናትህን አክብር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም። |
ስለዚህም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግር ወደ ንጉሡ ገባች፤ ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ እናቱን እጅ በመንሣት ተቀበላት፤ እርሱም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት፤
ኤልሳዕም ይህን ሁሉ እያየ “የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች የሆንክ አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ!” እያለ ወደ ኤልያስ ጮኸ፤ ከዚያም በኋላ ኤልያስን ዳግመኛ አላየውም። ኤልሳዕም ከሐዘን ብዛት የተነሣ ልብሱን ከሁለት ቀደደ፤
ከዚህ በኋላ እኔ ኤርምያስ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ለሬካባውያን ወገን የተናገረውን ቃል እንዲህ ብዬ ገለጥኩላቸው፦ “የቀድሞ አባታችሁ ኢዮናዳብ የሰጣችሁን ትእዛዝ ሁሉ ፈጽማችኋል፤ ትምህርቱንም ሁሉ ተከትላችኋል፤ ያዘዛችሁንም ሁሉ አድርጋችኋል፤
እንዲሁም መኖሪያ ቤት መሥራት፥ እርሻ ማረስ፥ የወይን ተክል ቦታዎችን ይዘን መንከባከብ እንደማይገባን ነግሮናል፤ እንደ እንግዶች በዚህች ምድር ለብዙ ጊዜ መቀመጥ እንችል ዘንድ በድንኳን መኖር እንደሚገባን አዞናል።
የሠራዊት አምላክ ካህናቱን እንዲህ ይላቸዋል፦ “ልጅ አባቱን፥ አገልጋይም አሳዳሪ ጌታውን ያከብራል፤ እነሆ፥ እኔ አባታችሁ ከሆንኩ ለምን አታከብሩኝም? ጌታችሁም ከሆንኩ ለምን ክብር አትሰጡኝም? እናንተ የእኔን ስም ንቃችኋል፤ ነገር ግን ‘ስምህን የናቅነው እንዴት ነው?’ ብላችሁ ትጠይቃላችሁ።
ትእዛዞችን ታውቃለህ፤ እነርሱም ‘አትግደል፤ አታመንዝር፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፤ አታታል፤ አባትህንና እናትህን አክብር፤’ የተባሉት ናቸው።”
ትእዛዞቹንም ብትጠብቁ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለዘሮቻቸው ሊሰጣቸው ቃል በገባላቸው በማርና በወተት በበለጸገችው፥ በዚያች ለምለም ምድር ለረጅም ዘመን ትኖራላችሁ።
ይህ ሕግ የባዶ ቃላት ቅንብር አይደለም፤ እርሱ የሕይወታችሁ መሠረት ነው፤ ስለዚህ ለዚህ ቃል ታዛዦች ሁኑ፤ ይህን ብታደርጉ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሱአት ምድር ለረዥም ዘመን ትኖራላችሁ።”
ይህን ብታደርጉ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርስዋት ምድር ረጅም ጊዜ እንደማትኖሩባትና በፍጹም እንደምትደመሰሱ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እነግራችኋለሁ።
እግዚአብሔር አምላካችሁ ለዘለዓለም እንድትኖሩባት በሚያወርሳችሁ ምድር ለረጅም ዘመን ትኖሩ ዘንድ ለእናንተና ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም እንዲሆንላቸው እኔ ዛሬ የማዛችሁን ሕጉንና ትእዛዞቹን ጠብቁ።”
“ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ባዘዝኩህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል።
በዚያች ምድር ለረጅም ዘመናት መኖር እንድትችሉ አንተና ልጆችህ፥ የልጅ ልጆችህም በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን መፍራትና እኔ ለሰጠኋችሁ ደንቦችና ትእዛዞች ታዛዦች መሆን ይገባችኋል።
ዳዊትም ከዚያ ተነሥቶ በሞአብ ወደምትገኘው ወደ ምጽጳ ሄደ፤ የሞአብንም ንጉሥ “እግዚአብሔር ለእኔ የሚያደርግልኝን ነገር እስካውቅ ድረስ እባክህ አባቴና እናቴ መጥተው በአንተ ዘንድ እንዲቈዩ ፍቀድላቸው” ሲል ጠየቀው።