በተራራው ዙሪያ ድንበር አብጅ፤ እነርሱም ያንን ድንበር አልፈው ወደ ተራራው እንዳይወጡና እንዲያውም ድንበሩን እንዳይነኩ ንገራቸው፤ ማንም ሰው ከተወሰነው ድንበር አልፎ፥ ተራራውን ቢነካ በሞት ይቀጣ፤
ዘፀአት 19:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም እንዲህ ሲል ለእግዚአብሔር መለሰ፦ “ቦታው ቅዱስ ስለ ሆነ ከዚህ ራቁ ብለህ ስለ አስጠነቀቅከን ሕዝቡ ወደ ተራራው ሊወጣ አይችልም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ሕዝቡ ወደ ሲና ተራራ ሊወጡ አይችሉም፤ ምክንያቱም አንተ ራስህ ‘በተራራው ዙሪያ ወሰን አድርግ፤ የተቀደሰም በማድረግ ለየው’ በማለት አስጠንቅቀኸናልና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ጌታን፦ “አንተ በተራራው ዙሪያ ወሰን አድርግ፥ ቀድሰውም ብለህ አስጠንቅቀኸናልና ሕዝቡ ወደ ተራራ ሊወጡ አይችሉም” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እግዚአብሔርን፥ “ሕዝቡ ወደ ሲና ተራራ ይወጡ ዘንድ አይችሉም፤ አንተ፦ በተራራው ዙሪያ ወሰን አድርግ፤ ቀድሰውም ብለህ አስጠንቅቀኸኛልና” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እግዚአብሔርን፦ አንተ፦ በተራራው ዙሪያ ወሰን አድርግ ቀድሰውም ብለህ አስጠንቅቀኸናልና ሕዝቡ ወደ ተራራ ይወጡ ዘንድ አይችሉም አለው። |
በተራራው ዙሪያ ድንበር አብጅ፤ እነርሱም ያንን ድንበር አልፈው ወደ ተራራው እንዳይወጡና እንዲያውም ድንበሩን እንዳይነኩ ንገራቸው፤ ማንም ሰው ከተወሰነው ድንበር አልፎ፥ ተራራውን ቢነካ በሞት ይቀጣ፤
እግዚአብሔርም “ውረድና አሮንን ይዘህ ና፤ ካህናቱም ሆኑ ሕዝቡ ወደ እኔ ለመውጣት ወሰኑን ማለፍ የለባቸውም፤ ይህን ቢያደርጉ ግን እኔ እግዚአብሔር እቀጣቸዋለሁ።”