ዘፀአት 19:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአገልግሎት ወደ እኔ የሚቀርቡ ካህናት እንኳ ሳይቀሩ ራሳቸውን ያንጹ፤ ይህ ካልሆነ እኔ እግዚአብሔር እቀጣቸዋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡት ካህናት እንኳ ራሳቸውን መቀደስ አለባቸው፤ አለዚያ እግዚአብሔር ቍጣውን ያወርድባቸዋል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ጌታ የሚቀርቡት ካህናትም ራሳቸውን ይቀድሱ ካልሆነ ግን ጌታ ያጠፋቸዋል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እግዚአብሔርም የሚቀርቡት ካህናት ደግሞ እንዳያጠፋቸው ራሳቸውን ይቀድሱ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እግዚአብሔርም የሚቀርቡት ካህናት ደግሞ እግዚአብሔር እንዳያጠፋቸው ራሳቸውን ይቀድሱ አለው። |
የሁለተኛው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን የበግ ጠቦቶችን ለፋሲካ በዓል መሥዋዕት አድርገው ዐረዱ፤ በዚህ ጊዜ ራሳቸውን ያላነጹ ካህናትና ሌዋውያን በጣም አፈሩ፤ ከዚህም የተነሣ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለዩ፤ ከዚያም በኋላ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ማቅረብ ቻሉ።
እግዚአብሔርም “ውረድና አሮንን ይዘህ ና፤ ካህናቱም ሆኑ ሕዝቡ ወደ እኔ ለመውጣት ወሰኑን ማለፍ የለባቸውም፤ ይህን ቢያደርጉ ግን እኔ እግዚአብሔር እቀጣቸዋለሁ።”
እናንተ የቤተ መቅደስን ንዋያተ ቅድሳት የተሸከማችሁ! ከባቢሎን ውጡ፤ ከእርሱም ተለዩ፤ ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋም ወጥታችሁ ራሳችሁን አንጹ።
የሚቃጠል መሥዋዕትና የምግብ መባ ለእኔ ለአምላካቸው የሚያቀርቡ ካህናት ለእኔ የተለዩና ስሜንም የማያረክሱ መሆን አለባቸው፤ ስለዚህ የተቀደሱ ይሆናሉ።
አሁንም ለሕዝቡ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ለነገ ራሳችሁን አንጹ፤ የምትበሉትም ሥጋ ይኖራችኋል፤ የምንበላውን ሥጋ ማን ይሰጠናል ብላችሁ ማልቀሳችሁንና የግብጽ ምድር ይሻለን ነበር ማለታችሁን እግዚአብሔር ሰምቶአል፤ እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር ሥጋ ይሰጣችኋል፤ እርሱንም ትበላላችሁ።