ዘፀአት 19:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔን እግዚአብሔርን ለማየት የተወሰነውን ክልል አልፈው እንዳይመጡ ወርደህ ለሕዝቡ ንገር፤ ይህን ቢያደርጉ ግን ከእነርሱ ብዙዎቹ ይሞታሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ሕዝቡ እግዚአብሔርን ለማየት በመጣደፍ ብዙዎቹ እንዳይጠፉ ውረድና አስጠንቅቃቸው መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ውረድ፥ ጌታን ለማየት ዳርቻውን እንዳያልፉና ከእነርሱም ብዙዎቹ እንዳይጠፉ ሕዝቡን አስጠንቅቃቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “ውረድ፤ ይህንም ለመረዳት ወደ እግዚአብሔር እንዳይቀርቡ፥ ከእነርሱም ብዙ እንዳይጠፉ ለሕዝቡ አስጠንቅቃቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ውረድ፥ እግዚአብሔርን ለማየት ዳርቻውን እንዳያልፉ ከእነርሱም ብዙ እንዳይጠፉ ለሕዝቡ አስጠንቅቃቸው፤ |
ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትገባበት ጊዜ ለአረማመድህ ጥንቃቄ አድርግ፤ እዚያ ሄዶ ደጉን ከክፉ ለይተው የማያውቁ ሞኞች ሰዎች እንደሚያደርጉት መሥዋዕት ከማቅረብ ይልቅ የምክር ቃላትን ለመስማት ዝግጁ ሆኖ መገኘት ይበልጣል።
ከሰፈር በሚነሡበትም ጊዜ አሮንና ልጆቹ ንዋያተ ቅድሳቱንና የእነርሱንም መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ የቀዓት ልጆች መጥተው ይሸከሙአቸው፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ ንዋያተ ቅድሳቱን መንካት አይገባቸውም፤ እንግዲህ የመገናኛው ድንኳን በሚነሣበት ጊዜ ሁሉ የቀዓት ልጆች ኀላፊነት ይህ ነው።
ወደ ተቀደሰው ስፍራ ተጠግተው እንዳይሞቱ እንዲህ አድርግላቸው፦ አሮንና ልጆቹ ወደ መቅደሱ ገብተው የያንዳንዱን ሰው ሥራና ሸክሙን ይመድቡለት።
እናንተ እሳቱን በመፍራት ወደ ተራራው መውጣት ስለ ፈራችሁ እኔ በዚያን ጊዜ እርሱ የሚለውን ሁሉ ልነግራችሁ በእናንተና በእግዚአብሔር መካከል ቆምኩ፤ “እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤
የታቦቱን ውስጣዊ ክፍል በመመልከታቸው እግዚአብሔር ተቈጥቶ ከቤት ሼሜሽ ሰዎች መካከል ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ እግዚአብሔርም ይህን ሁሉ እልቂት በመካከላቸው በማድረጉ የቤት ሼሜስ ሰዎች በማዘን አለቀሱ።