ዘፀአት 19:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይኸውም ማንም ሳይነካው በድንጋይ ተወግሮ ወይም በፍላጻ ተወግቶ ይገደል፤ ይህን የሚያደርጉ ሰዎችም ሆኑ እንስሶች በዚሁ ዐይነት ይገደሉ፤ ሕዝቡ ወደ ተራራው መውጣት የሚገባው ለረጅም ጊዜ መለከት ሲነፋ ብቻ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድንጋይ ይወገራል ወይም በቀስት ይወጋል፤ ምንም እጅ በርሱ ላይ አያርፍም፤ ሰውም ሆነ እንስሳ በሕይወት እንዲኖር አይተውም።’ ወደ ተራራው መውጣት የሚችሉት ከፍ ባለ ድምፅ መለከት በተነፋ ጊዜ ብቻ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማንም እጅ አይንካው፤ የሚነካው ግን በድንጋይ ይወገራል፥ ወይም በፍላጻ ይወጋል፤ እንስሳም ቢሆን፥ ሰውም ቢሆን አይድንም።’ ሳያቋርጥ የመለከት ድምፅ ሲነፋ በዚያን ጊዜ ወደ ተራራው ይውጡ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የማንም እጅ አይንካ፤ የሚነካውም ሁሉ በድንጋይ ይወገራል፤ ወይም በፍላጻ ይወጋል፤ እንስሳ ወይም ሰው ቢሆን የቀረበ አይድንም። የመለከት ድምፅና ደመና በተራራው በዐለፈ ጊዜ ወደ ተራራው ይውጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማንም እጅ አይንካ፤ ነገር ግን የሚነካው ሁሉ ይወገራል፥ ወይም በፍላጻ ይወጋል፤ እንስሳ ወይም ሰው ቢሆን አይድንም በላቸው። ሳያቍርጥ የመለከት ድምፅ ሲነፋ በዚያን ጊዜ ወደ ተራራው ይውጡ። |
በሦስተኛው ቀን ማለዳ የነጐድጓድ ድምፅ አስተጋባ፤ የመብረቅ ብልጭልጭታና ጥቅጥቅ ያለ ደመና በተራራው ላይ ታየ፤ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የእምቢልታ ድምፅ ተሰማ። ሰዎቹም በሰፈሩበት ቦታ ፈርተው ተንቀጠቀጡ።
ከአንተ ጋር ማንም ሰው አይምጣ፤ በተራራው በማንኛውም በኩል ቢሆን ማንም ሰው አይታይ፤ በግ ወይም ከብት ማንኛውም እንስሳ በተራራው ግርጌ አይሰማራ።”
የምንለወጠውም የመጨረሻው እምቢልታ በሚነፋበት ጊዜ እንደ ዐይን ቅጽበት በአንድ ጊዜ ነው። መለከቱ ይነፋል፤ የሞቱትም ሰዎች የማይጠፉ ሕያዋን ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን፤
የትእዛዝ ድምፅ፥ የመላእክት አለቃ ድምፅ፥ የእግዚአብሔር እምቢልታም ይሰማል፤ ጌታ ራሱም በእነዚህ ታጅቦ ከሰማይ ይወርዳል፤ በክርስቶስ አምነው የሞቱትም አስቀድመው ይነሣሉ።