“አንተም ዕዝራ፥ አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ ጥበብና ዕውቀት እየተመራህ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ሕግ የሚመሩትን፥ በኤፍራጥስ ማዶ የሚገኙትን ሰዎች የሚመሩ አስተዳዳሪዎችንና ዳኞችን ሹምላቸው፤ ለማያውቁትም ሁሉ የአምላክህን ሕግ አስተምራቸው፤
ዘፀአት 18:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ሁልጊዜ ተገኝተው ከባድ ያልሆኑ ጉዳዮችን በማየት በዳኝነት ሕዝቡን ያገልግሉ፤ ከአቅማቸው በላይ የሆነውን ከባድ ጉዳይ ወደ አንተ ያምጡት፤ እነርሱ በዚህ ዐይነት ሸክምህን ቢካፈሉልህ ሥራው ይቀልልሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማንኛውም ጊዜ ሕዝቡን ይዳኙ፤ ቀላሉን ነገር እነርሱ ይወስኑ፤ አስቸጋሪ የሆነውን ጕዳይ ሁሉ ግን ለአንተ እንዲያቀርቡ አድርግ፤ ሥራውን ስለሚያግዙህ ሸክምህ ይቃለላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕዝቡ ላይ ሁልጊዜ ይፍረዱ፤ ትልቁን ነገር ሁሉ ወደ አንተ ያምጡት፥ ትንሹንም ነገር ሁሉ እነርሱ ይፍረዱ፤ እነርሱም ከአንተ ጋር ሸክሙን ይሸከማሉ፥ ለአንተም ይቀልልሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሕዝቡ ላይ ሁል ጊዜ ይፍረዱ፤ የከበዳቸውን ነገር ወደ አንተ ያምጡት፤ ቀላሉን ነገር ሁሉ እነርሱ ይፍረዱ፤ ያቃልሉልሃል፤ ይረዱሃልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሕዝቡ ላይ ሁልጊዜ ይፍረዱ፤ አውራውን ነገር ሁሉ ወደ አንተ ያምጡት፥ ታናሹንም ነገር ሁሉ እነርሱ ይፍረዱ፤ እነርሱም ከአንተ ጋር ሸክሙን ይሸከማሉ፥ ለአንተም ይቀልልልሃል። |
“አንተም ዕዝራ፥ አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ ጥበብና ዕውቀት እየተመራህ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ሕግ የሚመሩትን፥ በኤፍራጥስ ማዶ የሚገኙትን ሰዎች የሚመሩ አስተዳዳሪዎችንና ዳኞችን ሹምላቸው፤ ለማያውቁትም ሁሉ የአምላክህን ሕግ አስተምራቸው፤
በዚህ ዐይነት ብትሠራና ይህም የእግዚአብሔር ፈቃድ ቢሆን ራስህን በከንቱ አታደክምም፤ ሕዝቡም በቀላሉ ጉዳዩ እየተፈጸመለት ወደየቤቱ ይሄዳል።”
እነርሱም ከባድ ያልሆኑ ጉዳዮችን በማየት ሕዝቡን ሁልጊዜ በዳኝነት ያገለግሉ ጀመር፤ አስቸጋሪ የሆኑትን ጉዳዮች ብቻ ወደ ሙሴ ሲያቀርቡ፥ ቀላል የሆነውን ጠብና ክርክር ሁሉ ራሳቸው ይወስኑ ነበር።
የእስራኤላዊቱ ልጅ የእግዚአብሔርን ስም ስለ ተሳደበ ወደ ሙሴ አቀረቡት፤ የእናቱም ስም ሰሎሚት የምትባልና ከዳን ነገድ የሆነው የዲብሪ ልጅ ነበረች።
እኔም ወደዚያ ወርጄ ከአንተ ጋር እነጋገራለሁ፤ ለአንተም ከሰጠሁህ መንፈስ ከፍዬ ለእነርሱ እሰጣቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ በእነዚህ ሕዝብ ላይ ያለህን ኀላፊነት በመሸከም ይረዱሃል፤ ከእንግዲህም ወዲህ ይህን ሁሉ ኀላፊነት ብቻህን አትሸከምም።
የዮሴፍ ልጅ ምናሴ የወለደው የማኪር ልጅ የገለዓድ ጐሣ የሆኑት የቤተሰብ አለቆች ወደ ሙሴና ወደ ሌሎቹም የእስራኤል ሕዝብ አለቆች ቀርበው እንዲህ አሉ፤