የምተማመነው በአንተ ስለ ሆነ በየጠዋቱ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ ሕይወቴን በዐደራ ለአንተ ስለ ሰጠሁ የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ።
ዘፀአት 18:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ የእግዚአብሔርን ሥርዓትና ሕግ ልታስተምራቸው፥ እንዲሁም እንዴት መኖርና ምን ማድረግ እንደሚገባቸውም ልትገልጥላቸው ይገባል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥርዐቶቹንና ሕጎቹን አስተምራቸው፤ እንዴት መኖር እንዳለባቸውና ምን መሥራት እንደሚገባቸው አሳያቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥርዓቱንና ሕጉን አስተምራቸው፥ የሚሄዱበትን መንገድና የሚያደርጉትን ሥራ አሳውቃቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርንም ሥርዐቱንና ሕጉን መስክርላቸው፤ የሚሄዱበትንም መንገድ፥ የሚያደርጉትንም ሥራ ሁሉ አሳያቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥርዓቱንም ሕጉንም አስተምራቸው፥ የሚሄዱበትን መንገድ የሚያደርጉትንም ሥራ ሁሉ አሳያቸው። |
የምተማመነው በአንተ ስለ ሆነ በየጠዋቱ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ ሕይወቴን በዐደራ ለአንተ ስለ ሰጠሁ የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ።
ከመንገድ ወጥታችሁ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ብትባዝኑ ከበስተኋላችሁ “ትክክለኛው መንገድ ይህ ነው! በዚህ ሂድ” የሚለውን ድምፅ ትሰማላችሁ።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “በየጐዳናው ቆማችሁ ተመልከቱ፤ ጥንታዊና መልካም የሆነችው መንገድ የትኛዋ እንደ ሆነች ጠይቃችሁ ተረዱ፤ ባገኛችኋትም ጊዜ በእርስዋ ሂዱ፤ በሰላምም ትኖራላችሁ።” ሕዝቡ ግን “በእርስዋ አንሄድም!” አሉ።
“የሰው ልጅ ሆይ! እኔ ለእስራኤል ሕዝብ ጠባቂ አድርጌሃለሁ፤ ስለዚህ እኔ የምናገረውን ቃል ስማ፤ የምሰጥህንም የማስጠንቀቂያ ቃል ንገራቸው።
ስለዚህ ብዙ ሕዝቦች እንዲህ ይላሉ፥ “ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ስለሚገኝ፥ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤተ መቅደስም እንሂድ፤ እርሱ ፈቃዱን እንድናደርግ ያስተምረናል፤ እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን።”
ይህም፥ ቤቱን ትቶ ወደ ሩቅ አገር የሄደውን ሰው ይመስላል፤ እርሱም እያንዳንዱን አገልጋይ በልዩ ልዩ የሥራ ኀላፊነት ላይ መደበ፤ ዘበኛውንም ተግቶ እንዲጠብቅ አዘዘው።
ከዚህ በኋላ ሙሴ ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “እስራኤል ሆይ፥ አሁን እንግዲህ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ ለመውረስ ያበቃችሁ ዘንድ የማስተምራችሁን ሕግና ሥርዓት አዳምጣችሁ በሥራ ላይ አውሉት።
“እግዚአብሔር አምላኬ እንድነግራችሁ ያዘዘኝን ሕግና ሥርዓት ሁሉ አስተምሬአችኋለሁ፤ እርስዋን ለመውረስ በምትገቡባት ምድር ስትኖሩ እነዚህን ትእዛዞች አክብሩ።
ሙሴም የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፥ ዛሬ የምነግራችሁን ሕግና ሥርዓት ሁሉ አድምጡ፤ በጥንቃቄም አጥንታችሁ እነዚህን ትእዛዞች ጠብቁ።
ስለዚህ ወደ እርሱ ቀርበህ እግዚአብሔር አምላካችን የሚለውን ሁሉ አዳምጥ፤ ተመልሰህም እርሱ ያለውን ሁሉ ንገረን፤ እኛም ሰምተን እንታዘዛለን።’
በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንዴት መኖር እንደሚገባችሁ ከእኛ ተምራችኋል፤ አሁንም የምትኖሩት እንዲሁ ነው፤ በጌታ በኢየሱስ ስም የምንለምናችሁና የምንመክራችሁም ከዚህ በፊት ካደረጋችሁት ይበልጥ እንድታደርጉ ነው።