La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 18:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን በዳኝነት ለማገልገል ተቀመጠ፤ ሕዝቡም በዙሪያው በመቆም አጨናንቀውት ከጠዋት እስከ ማታ ቈየ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን ለመዳኘት ተቀመጠ፤ እነርሱም በዙሪያው ከጧት እስከ ማታ ድረስ ቆሙ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን ሊፈርድ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም በሙሴ ፊት ከጥዋት እስከ ማታ ድረስ ቆመው ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በነ​ጋው ሙሴ በሕ​ዝቡ ሊፈ​ርድ ተቀ​መጠ፤ ሕዝ​ቡም በሙሴ ፊት ከጥ​ዋት እስከ ማታ ድረስ ቆመው ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴ በሕዝቡ ሊፈርድ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም በሙሴ ፊት ከጥዋት እስከ ማታ ድረስ ቆመው ነበር።

Ver Capítulo



ዘፀአት 18:13
9 Referencias Cruzadas  

ወደ ከተማም አደባባይ እየሄድኩ በሸንጎ እቀመጥ በነበረ ጊዜ፥


ከዚህም በኋላ የትሮ የሙሴ ዐማት በሙሉ የሚቃጠል ቊርባንና ሌላም ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አመጣ፤ አሮንና የእስራኤል አለቆችም ሁሉ የተቀደሰውን ምግብ በአምልኮት ሥርዓት በእግዚአብሔር ፊት ለመመገብ ከሙሴ ዐማት ጋር መጡ።


የሙሴ ዐማት የትሮም ለሕዝቡ ያደርገው የነበረውን ሁሉ ከተመለከተ በኋላ እንዲህ ሲል ጠየቀው “ይህ ሁሉ ለሕዝቡ የምታደርገው ነገር ምንድን ነው? ሕዝቡ አንተን ለማነጋገር በመፈለግ ከጠዋት እስከ ማታ በዙሪያህ በመቆም እንደዚህ የሚያጨናንቅህና አንተም ይህን ሁሉ ጉዳይ በዳኝነት ለማየት ብቻህን የምትቀመጠው ለምንድነው?”


በዚያን ጊዜ አንድ መንግሥት በዘለዓለማዊ ፍቅር ይመሠረታል፤ በዙፋኑም ላይ ከዳዊት ዘር አንድ ታማኝ የሆነ፥ ፍትሕን የሚፈልግና ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ፈጣን የሆነ ንጉሥ ይቀመጥበታል።


“አሕዛብ ሁሉ ተነሣሥተው ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆ ይሂዱ፤ እኔ እግዚአብሔር በዙሪያ ባሉት አሕዛብ ላይ ለመፍረድ እዚያ እቀመጣለሁ።


“የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ለማስተማር በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።


ስጦታችን መምከር ከሆነ እንምከር፤ ስጦታችን መለገሥ ከሆነ ከልብ እንለግሥ፤ ስጦታችን ማስተዳደር ከሆነ በትጋት እናስተዳድር፤ ስጦታችን ርኅራኄ ማድረግ ከሆነ ይህንኑ በደስታ እናድርግ።


ግብር የምትከፍሉትም ስለዚህ ነው፤ ባለሥልጣኖች በዚህ ሥራ ላይ የተሰማሩት እግዚአብሔርን ለማገልገል ነው።


እናንተ ኮርቻ በተጫኑ በነጫጭ አህዮች ላይ ተቀምጣችሁ የምትጓዙ፥ እናንተ በምቹና በአማረ ግላስ ላይ የምትንደላቀቁ፥ እናንተ በእግር የምትንሸራሸሩ፥ ስለዚህ ነገር ተናገሩ።