ዘፀአት 18:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግብጻውያን በእስራኤል ሕዝብ ላይ ታብየው ያን ያኽል አሳፋሪ ድርጊት በመፈጸማቸው ይህን ሁሉ አስደናቂ ነገር ስላደረገ እነሆ፥ እኔም እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ የሚበልጥ መሆኑን አሁን ዐወቅሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ በላይ ኀያል እንደ ሆነ አሁን ዐወቅሁ፤ እስራኤልን በትዕቢት ይዘው በነበሩት ሁሉ ላይ ይህን አድርጓልና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በትዕቢት ባደረጉባቸው ነገር ላይ ጌታ ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ አሁን አወቅሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ግብፃውያን ከሚመኩባቸውና ከሚገዙላቸው አማልክት ሁሉ እንዲበልጥ አሁን ዐወቅሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትዕቢት ባደረጉባቸው ነገር እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ እንዲበልጥ አሁን አወቅሁ አለ። |
ከዚህም በኋላ ከተከታዮቹ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሶ መጥቶ፦ “ከእስራኤል አምላክ በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እነሆ፥ አሁን ተረዳሁ፤ ስለዚህም ጌታዬ ሆይ፥ እባክህ ይህን ስጦታ ተቀበለኝ” አለው።
በግብጽ ንጉሥ ላይ በባለሥልጣኖቹና በምድሩ በሚኖሩትም ሕዝብ ሁሉ ላይ ድንቅ ተአምራትን ገልጠህ አሳየህ። ይህንንም ያደረግኸው የቀድሞ አባቶቻችን እንዴት እንደሚጨቈኑ በማየትህ ነው፤ ይህንንም በማድረግህ እስከ ዛሬ ድረስ ዝናህ የገነነ ሆኖአል።
እነርሱም ወደ ሕግህ እንዲመለሱ አስጠነቀቅኻቸው፤ በትዕቢታቸው ግን ትእዛዞችህን ናቁ፤ ቢፈጽሙአቸው ሕይወት በሚሰጡት ሕጎችህ ላይ ኃጢአት ሠሩ። በልበ ደንዳናነት ፊታቸውን አዞሩ፤ በእልኸኛነታቸውም እምቢተኞች ሆኑ።
ከዚህም የተነሣ ከጠላቶቻችን ጋር ተባብረው ከወጉን በኋላ ከአገሪቱ አምልጠው መሄድ ይችላሉ፤ ስለዚህ ቊጥራቸው እየበዛ እንዳይሄድ ኑ፤ አንድ ዘዴ እንፈልግ።”
“የዕብራውያንን ሴቶች በምታዋልዱበት ጊዜ የሚወለደው ሕፃን ወንድ ከሆነ ወዲያውኑ ግደሉት፤ ሴት ከሆነች ግን በሕይወት እንድትኖር ተዉአት”።
ከዚህም በኋላ ንጉሡ “ከዕብራውያን የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ እያነሣችሁ ዓባይ ወንዝ ውስጥ ጣሉ፤ ሴቶች ልጆች ግን በሕይወት ይኑሩ” ሲል ለሕዝቡ ጥብቅ ትእዛዝ አስተላለፈ።
ስለዚህ ሙሴና አሮን ወደ ንጉሡ ሄደው እንዲህ አሉት፤ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለእኔ መታዘዝን እምቢ የምትለው እስከ መቼ ነው? አሁንም ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ፤
“በዚያችም ሌሊት እኔ በግብጽ ምድር ሁሉ እየተላለፍኩ እያንዳንዱን የሰውም ሆነ የእንስሳ ዘር የሆነውን የበኲር ልጅ ሁሉ እገድላለሁ፤ የግብጽንም አማልክት ሁሉ እቀጣለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
“አምላክ ሆይ፥ ከአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅድስናስ እንደ አንተ ያለ ባለግርማ ማን ነው? አንተ ያደረግሃቸውን ተአምራትና አስገራሚ ሥራዎች ሊያደርግ የሚችልስ ማን አለ?
ንጉሡም “ለመሆኑ እግዚአብሔር ማን ነው? የእርሱንስ ትእዛዝ ሰምቼ እስራኤልን የምለቀው ለምንድን ነው? እኔ እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም አለቅም” አለ።
“እነሆ፥ እኔ ናቡከደነፆር ለሰማይ ንጉሥ ምስጋና፥ ክብርና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ መንገዱም ፍትሓዊ ነው፤ በትዕቢት የሚመሩትንም ሁሉ ማዋረድ ይችላል።”
ግብጻውያን በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር መቅሠፍት የሞቱትን የበኲር ልጆቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ እግዚአብሔርም በአማልክታቸው ላይ እንኳ ፈርዶአል።
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።
እስቲ በመታበይ አትጓደዱ፤ የትምክሕት ንግግራችሁንም አስወግዱ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሁሉን ያውቃል፤ ሕዝብ የሚሠራውንም ሁሉ በፍርድ ይመዝናል።