ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ዛሬውኑ ብሉት፤ ዛሬ ሰንበት ስለ ሆነና እርሱም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ቀን በመሆኑ በዛሬው ዕለት ምግቡን በሜዳ ላይ አታገኙም።
ዘፀአት 16:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ስድስት ቀን በተከታታይ ይህን ምግብ ሰብስቡ፤ የዕረፍት ቀን በሆነው በሰባተኛው ቀን ግን ምንም ምግብ አይኖርም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስድስት ቀን ትሰበስቡታላችሁ፤ በሰባተኛው ቀን በሰንበት ዕለት ግን ምንም ነገር አይኖርም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስድስት ቀን ትሰበስባላችሁ ሰባተኛው ቀን ግን ሰንበት ነው፤ በእርሱ አይኖርም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድስት ቀን ልቀሙት፤ ሰባተኛው ቀን ግን ሰንበት ነው፤ በእርሱ አይገኝም” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስድስት ቀን ልቀሙት ሰባተኛው ቀን ግን ሰንበት ነው፤ በእርሱ አይገኝም አለ። |
ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ዛሬውኑ ብሉት፤ ዛሬ ሰንበት ስለ ሆነና እርሱም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ቀን በመሆኑ በዛሬው ዕለት ምግቡን በሜዳ ላይ አታገኙም።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባው ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ የሚያመለክተው በር በስድስቱ የሥራ ቀኖች ዝግ መሆን አለበት፤ ነገር ግን በሰንበት ቀንና በየወሩ መባቻ ቀን ይከፈታል።
ኢየሱስ በሰንበት ቀን ስለ ፈወሰ የምኲራቡ አለቃ ተቈጣና ለሕዝቡ፦ “በሳምንት ውስጥ ሥራ የሚሠራባቸው ስድስት ቀኖች አሉ፤ በእነዚህ ቀኖች እየመጣችሁ ተፈወሱ፤ በሰንበት ቀን ግን አይሆንም” ብሎ ተናገረ።