ዘፀአት 16:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ዛሬውኑ ብሉት፤ ዛሬ ሰንበት ስለ ሆነና እርሱም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ቀን በመሆኑ በዛሬው ዕለት ምግቡን በሜዳ ላይ አታገኙም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም እንዲህ አለ፤ “ዛሬውኑ ብሉት፤ ዛሬ የእግዚአብሔር ሰንበት ነውና። ዛሬ በመሬት ላይ ምንም አታገኙም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም፦ “ዛሬ ብሉት፥ ዛሬ ለጌታ ሰንበት ነውና፤ ዛሬ በሜዳ አታገኙትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም፥ “የእግዚአብሔር ሰንበት ዛሬ ነውና ብሉት፤ ዛሬ በሜዳ አታገኙትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም፦ የእግዚአብሔር ሰንበት ዛሬ ነውና ብሉት፤ ዛሬ በሜዳ አታገኙትም። |
እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “የነገው ዕለት ለእርሱ ተለይቶ የተቀደሰ የዕረፍት ቀን እንዲሆን እግዚአብሔር አዞአል፤ ስለዚህ ዛሬውኑ የምትጋግሩትን ጋግሩ፤ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፤ የተረፈው ተከፍሎ ለነገ ይቀመጥ።”
እኔ አንድ የዕረፍት ቀን ሰጥቻችኋለሁ፤ ዘወትር በስድስተኛው ቀን ለሁለት ቀን የሚበቃ ምግብ ስለምሰጣችሁ በሰባተኛው ቀን እያንዳንዱ ሰው ከቤት ሳይወጣ፥ ባለበት ስፍራ ሁሉ ዕረፍት አድርጎ ይዋል።”