አንዳንዶቹ የሙሴን ቃል ባለመስማት ለዕለቱ ከሰበሰቡት ከፍለው አሳደሩ፤ በማግስቱም ጠዋት ተልቶ ተገኘ፤ በስብሶም ሸተተ፤ ሙሴም እጅግ ተቈጣቸው።
ዘፀአት 16:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም እንዳዘዛቸው የተረፈውን ለሚቀጥለው ቀን አስቀመጡ፤ እርሱም አልሸተተም ወይም አልተላም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሙሴ እንዳዘዘው እስከ ጧት ድረስ አቈዩት፤ አልሸተተም፤ ወይም አልተላም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም እንዳዘዘ ለጥዋት አስቀመጡት፤ አልሸተተም፥ ትልም አልነበረበትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እንደ አዘዘ ለነገ አኖሩት፤ አልሸተተም፤ ትልም አልሆነበትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እንዳዘዘ ለነገ አኖሩት፤ አልሸተተም፥ ትልም አልሆነበትም። |
አንዳንዶቹ የሙሴን ቃል ባለመስማት ለዕለቱ ከሰበሰቡት ከፍለው አሳደሩ፤ በማግስቱም ጠዋት ተልቶ ተገኘ፤ በስብሶም ሸተተ፤ ሙሴም እጅግ ተቈጣቸው።
ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ዛሬውኑ ብሉት፤ ዛሬ ሰንበት ስለ ሆነና እርሱም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ቀን በመሆኑ በዛሬው ዕለት ምግቡን በሜዳ ላይ አታገኙም።
ሙሴም አሮንን “አንድ የሸክላ ዕቃ ወስደህ አንድ ኪሎ ተኩል በሚይዝ መስፈሪያ መና አኑርበት፤ ለመጪውም ትውልድ በእግዚአብሔር ፊት ተጠብቆ እንዲኖር አድርግ” አለው።