ወደ ሲና ተራራ ወርደህ ከሰማይ ሕዝብህን አነጋገርካቸው፤ ትክክለኛና ፍትሓዊ ሕግንና ሥርዓትን፥ መልካም የሆኑትን ደንቦችንና ትእዛዞችን ሰጠሃቸው።
ዘፀአት 16:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “የነገው ዕለት ለእርሱ ተለይቶ የተቀደሰ የዕረፍት ቀን እንዲሆን እግዚአብሔር አዞአል፤ ስለዚህ ዛሬውኑ የምትጋግሩትን ጋግሩ፤ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፤ የተረፈው ተከፍሎ ለነገ ይቀመጥ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም አላቸው፤ “እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፤ ‘ነገ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሰንበት በመሆን፣ የዕረፍት ቀን ይሆናል።’ ስለዚህ መጋገር የምትፈልጉትን ጋግሩ፤ መቀቀል የምትፈልጉትን ቀቅሉ። የተረፈውን አስቀምጡ፤ እስከ ጧትም ድረስ አቈዩት።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ የተናገረው ይህ ነው፦ ነገ የዕረፍት ሰንበት ነው፥ ለጌታ የተቀደሰ ሰንበት ነው፤ የምትጋግሩትን ጋግሩ፥ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፥ የተረፈውን ሁሉ ተውት ለጥዋት ለእናንተ አስቀምጡት።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም፥ “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው፦ ነገ ዕረፍት፥ ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ሰንበት ነው፤ ነገ የምትጋግሩትን ዛሬ ጋግሩ፤ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፤ የተረፈውንም ሁሉ ለነገ እንዲጠበቅ አኑሩ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው፦ ነገ ዕረፍት፥ ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ሰንበት ነው፤ የምትጋግሩትን ጋግሩ፥ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፥ የተረፈውን ሁሉ ለነገ እንዲጠበቅ አኑሩት አላቸው። |
ወደ ሲና ተራራ ወርደህ ከሰማይ ሕዝብህን አነጋገርካቸው፤ ትክክለኛና ፍትሓዊ ሕግንና ሥርዓትን፥ መልካም የሆኑትን ደንቦችንና ትእዛዞችን ሰጠሃቸው።
“በሳምንት ስድስት ቀን ሥራህን ሁሉ ሥራ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ምንም ሥራ አትሥራበት፤ በዚህ ዐይነት አገልጋዮችህና ለአንተ የሚሠሩ መጻተኞች፥ እንዲሁም በሬህና አህያህ ዕረፍት አድርገው ይዋሉ።
ሥራችሁን ሁሉ የምታከናውኑባቸው ስድስት የሥራ ቀኖች አሉላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእኔ ተለይቶ የተቀደሰ የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚህ ቀን ሥራ የሚሠራበት ሁሉ በሞት ይቀጣ።
የቀድሞ አባቶቻችሁን እንዳዘዝኳቸው ሰንበትን የተቀደሰ ቀን አድርጋችሁ አክብሩ እንጂ በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ ከቤታችሁ አትውጡ፤ በሰንበት ቀን ምንም ሥራ አትሥሩ።
ሥራ የምትሠሩባቸው ስድስት ቀኖች አሉላችሁ፤ ሰባተኛው ዕለተ ሰንበት ግን የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ለአምልኮ ተሰብሰቡ እንጂ ምንም ሥራ አትሥሩበት፤ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ሰንበት ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕለት ነው፤
ሰዎቹም እየዞሩ ይለቅሙ ነበር፤ በወፍጮም ይፈጩት ወይም በሙቀጫ ይወቅጡት፥ በምንቸትም ያፈሉትና ይጋግሩት ነበር፤ ጣዕሙም በዘይት እንደ ተለወሰ ቂጣ ነበር፤