አንዳንዶቹ የሙሴን ቃል ባለመስማት ለዕለቱ ከሰበሰቡት ከፍለው አሳደሩ፤ በማግስቱም ጠዋት ተልቶ ተገኘ፤ በስብሶም ሸተተ፤ ሙሴም እጅግ ተቈጣቸው።
ዘፀአት 16:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየማለዳው እያንዳንዱ የሚበቃውን ያኽል ይሰበስብ ነበር፤ ፀሐይ ከሞቀ በኋላ ግን በመሬት ላይ የቀረው ሁሉ ይቀልጥ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየማለዳው እያንዳንዱ የሚያስፈልገውን ያህል ሰበሰበ፤ ፀሓዩ እየበረታ በሄደም ጊዜ ቀለጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥዋት ጥዋት እያንዳንዱ የሚበላውን ያህል ሰበሰበ፤ ፀሐይም በሞቀ ጊዜ ቀለጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውም ሁሉ ለየራሱ ጥዋት ጥዋት ሰበሰበ፤ ፀሐይም በተኰሰ ጊዜ ቀለጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም ሁሉ ዕለት ዕለት የሚበላውን ያህል በጥዋት ለቀመ፤ ፀሐይም በተኮሰ ጊዜ ቀለጠ። |
አንዳንዶቹ የሙሴን ቃል ባለመስማት ለዕለቱ ከሰበሰቡት ከፍለው አሳደሩ፤ በማግስቱም ጠዋት ተልቶ ተገኘ፤ በስብሶም ሸተተ፤ ሙሴም እጅግ ተቈጣቸው።
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ብርሃን አለ፤ ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።
እግዚአብሔር፦ “ተስማሚ በሆነ ጊዜ ሰማሁህ! በመዳን ቀን ረዳሁህ!” ስለሚል፥ “እነሆ ተስማሚ የሆነው ጊዜ አሁን ነው፤ የመዳኛው ቀን አሁን ነው።”