ኤልሳዕም ወደ ግያዝ መለስ ብሎ “በፍጥነት ተነሥና የእኔን ምርኲዝ ይዘህ ሂድ! ለአንድም ሰው ሰላምታ ለመስጠት እንኳ በመንገድ አትቁም፤ ማንም ሰው ሰላምታ ቢሰጥህ አጸፋውን ለመመለስ ጊዜ አታጥፋ፤ በቀጥታ ወደ ቤት ሄደህ የእኔን ምርኲዝ በልጁ ፊት ላይ አኑር!” አለው።
ዘፀአት 14:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በትርህን አንሣ፤ በባሕሩም ላይ ዘርጋው፤ ውሃውም ከሁለት ይከፈላል፤ እስራኤላውያንም በደረቅ ምድር ባሕሩን አቋርጠው ይሄዳሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውሃውን ለመክፈል በትርህን አንሣና እጅህን በባሕሩ ላይ ዘርጋ፤ እስራኤላውያን በባሕሩ ውስጥ በየብስ ይሻገራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም በትርህን አንሣ፥ እጅህንም በባህሩ ላይ ዘርጋ፥ ክፈለውም፤ የእስራኤልም ልጆች በባህሩ ውስጥ በደረቅ ምድር ያልፋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም በትርህን አንሣ፤ እጅህንም በባሕሩ ላይ ዘርጋ፤ ክፈለውም፤ የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ ውስጥ በየብስ ያልፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም በትርህን አንሣ፤ እጅህንም በባህሩ ላይ ዘርጋ፤ ክፈለውም፤ የእስራኤልም ልጆች በባህሩ ውስጥ በየብስ ያልፋሉ። |
ኤልሳዕም ወደ ግያዝ መለስ ብሎ “በፍጥነት ተነሥና የእኔን ምርኲዝ ይዘህ ሂድ! ለአንድም ሰው ሰላምታ ለመስጠት እንኳ በመንገድ አትቁም፤ ማንም ሰው ሰላምታ ቢሰጥህ አጸፋውን ለመመለስ ጊዜ አታጥፋ፤ በቀጥታ ወደ ቤት ሄደህ የእኔን ምርኲዝ በልጁ ፊት ላይ አኑር!” አለው።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤል ሕዝብ አለቆች፥ ጥቂቶቹን ውሰድ፤ ከሕዝቡም ቀድመህ ወደ ፊት ሂድ፤ የዐባይን ወንዝ የመታህበትንም በትር በእጅህ ያዝ፤
እነሆ፥ እኔ በሲና ተራራ በአለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ አንተም አለቱን ምታው፤ ሕዝቡም የሚጠጡት ውሃ ከውስጡ ይፈልቃል፤” ሙሴም በእስራኤል አለቆች ፊት እንደዚሁ አደረገ።
ስለዚህም ሙሴ ሚስቱንና ወንዶች ልጆቹን በአህያ ላይ አስቀምጦ ወደ ግብጽ መጓዝ ጀመረ፤ ተአምራት የሚገለጥበት የእግዚአብሔርንም በትር በእጁ ይዞ ነበር።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አሮን በትሩን ወስዶ በግብጽ ምድር በሚገኙት ወንዞች፥ ቦዮችና ኲሬዎች ሁሉ ላይ እንዲዘረጋ ንገረው፤ በዚያን ጊዜ ውሃው ሁሉ ተለውጦ ደም ይሆናል፤ ከእንጨትና ከድንጋይ በተሠሩት የውሃ ማጠራቀሚያ ዕቃዎች እንኳ ሳይቀር በግብጽ ምድር የሚገኘው ውሃ ሁሉ ደም ይሆናል።”
“ፈርዖን ‘እስቲ ተአምራት በማድረግ ማንነታችሁን ግለጡልኝ’ ቢላችሁ ለአሮን ንገረውና በትሩን ወስዶ በንጉሡ ፊት ይጣለው፤ በዚያን ጊዜ በትሩ ተለውጦ እባብ ይሆናል።”
እኔ የሠራዊት አምላክ በዖሬብ አለት አጠገብ በምድያማውያን ላይ እንዳደረግሁት አሦራውያንን የምቀጣበት ጅራፍ ባሕሩን በበትሬ መትቼ ግብጻውያንን እንደቀጣሁ አሦራውያንን እቀጣለሁ። በግብጽ ላይ በትሬን እንዳነሣሁ በኤፍራጥስ ወንዝ ላይም አነሣለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! ፈረሶችህንና ሠረገላዎችህን ወደ ድል በመራኸቸው ጊዜ፥ ኀይለኛው ቊጣህ በወንዞች ላይ ነበርን? ወይስ በባሕሩ ላይ ተቈጥተህ ነበርን?
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ኢያሱን፦ “ጦርህን በዐይ ከተማ ላይ አንሣ፤ እኔ እርስዋን ለአንተ አሳልፌ እሰጥሃለሁ” አለው። ኢያሱም በእጁ ያለውን ጦር ወደ ከተማይቱ ዘረጋ።