ዘፀአት 12:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ይህን በዓል ያክብረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በዓሉን ማክበር ይኖርበታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ጉባኤ ሁሉ ያድርጉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ማኅበር ሁሉ ያድርጉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ጉባኤ ሁሉ ያድርጉት። |
ንጹሕ የሆነ እና ወደ ሩቅ አገር ያልሄደ ማንኛውም ሰው የፋሲካን በዓል በወቅቱ ባያከብር ከሕዝቤ ይለይ፤ መባውን በተወሰነው ጊዜ ባለማቅረቡ፥ ስለ ኃጢአቱ ተገቢውን ቅጣት ይቀበላል።
“በእናንተ መካከል መጻተኛ የእግዚአብሔርን ፋሲካ በዓል ለማክበር ቢፈልግ በተወሰነው ደንብና የሥርዓት መመሪያ ሁሉ መሠረት ማክበር ይኖርበታል፤ የአገር ተወላጁም ሆነ መጻተኛ ይህን ደንብ በተመሳሳይ ሁኔታ ይፈጽም።”