ዘፀአት 12:45 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ በሀገር ውስጥ የሚኖር እንግዳ ሰው ወይም አዲስ ቅጥር ሠራተኛ አይብላ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ለጊዜው የተቀመጠ እንግዳና ቅጥር ሠራተኛ መብላት የለበትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዳና ደሞዝተኛ ግን ከእርሱ አይብላ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥገኛና ሞያተኛ ግን ከእርሱ አይብሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጻተኛና ሞያተኛ ግን ከእርሱ አይብሉ። |
“ከተቀደሰው ስጦታ መብላት የሚችለው የካህን ቤተሰብ የሆነ ሰው ብቻ ነው፤ ሌላ ሰው ግን ከእርሱ አይብላ፤ ከካህኑ ጋር በእንግድነት ወይም ተቀጥሮ የሚኖር አይብላ።
እናንተ ከእስራኤል ማኅበረሰብ ግንኙነት የሌላችሁ፥ ለተስፋው ቃል ኪዳን እንግዶች የሆናችሁ፥ በዚህ ዓለምም አንዳች ተስፋ የሌላችሁ፥ ያለ እግዚአብሔር የምትኖሩ፥ ከክርስቶስም የተለያችሁ እንደ ነበራችሁ አስታውሱ።