እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት አብርሃም በዚያኑ ቀን ልጁን እስማኤልን ገረዘው፤ እንዲሁም በቤቱ ውስጥ የተወለዱና ከውጪ የተገዙ ባሪያዎች ሳይቀሩ፥ በቤቱ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ገረዘ፤
ዘፀአት 12:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሪያ እንዲሆናችሁ በገንዘባችሁ የገዛችሁት ሰው ግን አስቀድማችሁ ከገረዛችሁት በኋላ መብላት ይችላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በገንዘብ የገዛኸው ማንኛውም ባሪያ ከገረዝኸው በኋላ መብላት ይችላል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በብር የተገዛ የማንም ባርያ ቢኖር ከተገረዘ በኋላ ከእርሱ ይብላ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አገልጋይ ወይም በብር የተገዛ ቢኖር ከተገረዘ በኋላ ያን ጊዜ ከእርሱ ይብላ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በብር የተገዛ ባሪያ ቢኖር ከተገረዘ በኋላ ከእርሱ ይብላ። |
እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት አብርሃም በዚያኑ ቀን ልጁን እስማኤልን ገረዘው፤ እንዲሁም በቤቱ ውስጥ የተወለዱና ከውጪ የተገዙ ባሪያዎች ሳይቀሩ፥ በቤቱ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ገረዘ፤