ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በግብጽ ንጉሥና በሕዝቡም ሁሉ ላይ ሌላ መቅሠፍት እልካለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከዚህች ምድር እንድትወጡ ይለቃችኋል፤ እንዲያውም አንድ ሳይቀር ሁላችሁንም ያባርራችኋል።
ዘፀአት 12:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከግብጽ በድንገት ተጣድፈው ስለ ወጡ ምግባቸውን ለማዘጋጀትም ሆነ በእርሾ የቦካ እንጀራ ለመጋገር ጊዜ ስላልነበራቸው ከግብጽ ይዘው ካወጡትም ሊጥ ቂጣ ጋገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከግብጽ ይዘው ከወጡት ሊጥ ያልቦካ ቂጣ ጋገሩ፤ ሊጡ አልቦካም ነበር፤ ምክንያቱም ከግብጽ በጥድፊያ እንዲወጡ ስለተደረጉ፣ ለራሳቸው ምግብ ለማዘጋጀት ጊዜ አልነበራቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግብጽም ከእነርሱ ጋር ያወጡትን ሊጥ ጋገሩ፥ አልቦካም ነበርና ቂጣ አደረጉት፤ ግብፃውያን በመውጣት ስላስቸኮሉአቸው ይቆዩ ዘንድ አልተቻላቸውም፥ ስንቅም አላሰናዱም ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግብፅም ከእነርሱ ጋር ያወጡትን ሊጥ ቂጣ እንጎቻ አድርገው ጋገሩት። አልቦካም ነበርና፤ ግብፃውያንም ስለ አስወጡአቸው ይቈዩ ዘንድ አልተቻላቸውምና፤ ለመንገድም ስንቅ አላሰናዱም ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግብፅም ከእነርሱ ጋር ያወጡትን ሊጥ ጋገሩ፤ አልቦካም ነበርና ቂጣ እንጎቻ አደረጉት፤ ግብፃውያን በመውጣት ስላስቸኮሉአቸው ይቆዩ ዘንድ አልተቻላቸውም፤ ስንቅም አላሰናዱም ነበር። |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በግብጽ ንጉሥና በሕዝቡም ሁሉ ላይ ሌላ መቅሠፍት እልካለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከዚህች ምድር እንድትወጡ ይለቃችኋል፤ እንዲያውም አንድ ሳይቀር ሁላችሁንም ያባርራችኋል።
እግዚአብሔርም ሙሴን “በንጉሡ በፈርዖን ላይ የማደርገውን አሁን ታያለህ፤ በኀይሌ ተገዶ ሕዝቤን ይለቃል፤ በኀያል ክንዴም ተሸንፎ ያባርራቸዋል።”
ደግሞም ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፦ “መንግሥተ ሰማይ አንዲት ሴት ወስዳ ከሦስት መስፈሪያ ዱቄት ጋር የለወሰችውን እርሾ ትመስላለች፤ እርሾውም ሊጡን ሁሉ እንዲቦካ አደረገው።”