ዘፀአት 12:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያኑ ሌሊት ንጉሡ ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተና እስራኤላውያን ወገኖቻችሁ ሁሉ ከዚህ ውጡ! አገሬን ለቃችሁ ሂዱ! በጠየቃችሁትም መሠረት ለእግዚአብሔር ስገዱ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን ሌሊቱን አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ተነሡ፤ እናንተና እስራኤላውያን ከሕዝቤ መካከል ውጡ፤ ሂዱ፤ በጠየቃችሁት መሠረት እግዚአብሔርን አምልኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴንና አሮንን በሌሊት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእስራኤልም ልጆች ተነሡ፥ ከሕዝቤ መካከል ውጡ፤ ሂዱም፤ እንዳላችሁትም ጌታን አገልግሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በሌሊት ጠርቶ አላቸው፥ “እናንተ የእስራኤልም ልጆች ተነሡ፤ ከሕዝቤ መካከል ውጡ፤ ሂዱም፤ እንዳላችሁም እግዚአብሔርን አምልኩት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በሌሊት ጠርቶ፥ “እናንተ የእስራኤልም ልጆች ተነሡ፤ ከሕዝቤ መካከል ውጡ፤ ሂዱም፤ እንዳላችሁም እግዚአብሔርን አገልግሉ፤ |
ሙሴም “ሕፃን ልጆቻችንና ሽማግሌዎቻችን ሳይቀሩ ሁላችንም እንሄዳለን፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንን፥ በጎቻችንንና ፍየሎቻችንን፥ የቀንድ ከብቶቻችንንም ሁሉ እንወስዳለን፤ በምንሄድበት ስፍራ ለእግዚአብሔር በዓል እናደርጋለን” ሲል መለሰ።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በግብጽ ንጉሥና በሕዝቡም ሁሉ ላይ ሌላ መቅሠፍት እልካለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከዚህች ምድር እንድትወጡ ይለቃችኋል፤ እንዲያውም አንድ ሳይቀር ሁላችሁንም ያባርራችኋል።
ሙሴም “መኳንንትህ ሁሉ ወደ እኔ መጥተው እጅ ይነሡኛል፤ ሕዝቤንም ይዤ እንድወጣ ይለምኑኛል፤ ከዚያም በኋላ እሄዳለሁ” በማለት ንግግሩን አበቃ፤ ይህንንም ከተናገረ በኋላ በታላቅ ቊጣ ከንጉሡ ፊት ወጥቶ ሄደ።
ከግብጽ በድንገት ተጣድፈው ስለ ወጡ ምግባቸውን ለማዘጋጀትም ሆነ በእርሾ የቦካ እንጀራ ለመጋገር ጊዜ ስላልነበራቸው ከግብጽ ይዘው ካወጡትም ሊጥ ቂጣ ጋገሩ።
እግዚአብሔርም ሙሴን “በንጉሡ በፈርዖን ላይ የማደርገውን አሁን ታያለህ፤ በኀይሌ ተገዶ ሕዝቤን ይለቃል፤ በኀያል ክንዴም ተሸንፎ ያባርራቸዋል።”
ንጉሡም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “ጓጒንቸሮቹን ከእኔና ከሕዝቤ ዘንድ እንዲያርቅ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ፤ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ ሕዝባችሁን እለቃለሁ” አላቸው።
የግብጽ ንጉሥና ግብጻውያን እንዳደረጉት ስለምን ልባችሁን ታደነድናላችሁ? እስራኤላውያን የግብጽን ምድር ለቀው የወጡት፥ እግዚአብሔር ግብጻውያንን በብርቱ ከቀጣቸው በኋላ አልነበረምን?