ዘፀአት 12:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ አለቆች ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ቤተሰባችሁ ሁሉ የፋሲካን በዓል እንዲያከብር ከእናንተ እያንዳንዱ ጠቦት መርጦ ይረድ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ አለቆች በሙሉ አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ቶሎ ሄዳችሁ ለየቤተ ሰቦቻችሁ የሚሆን ጠቦት መርጣችሁ የፋሲካን በግ ዕረዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ሂዱ ለራሳችሁና ለቤተሰቦቻችሁ በግ ውሰዱ፥ ለፋሲካም እረዱት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም የእስራኤልን ልጆች ሽማግሌዎች ጠርቶ አላቸው፥ “ሂዱና በየወገናችሁ ጠቦት ውሰዱ፤ ለፋሲካም እረዱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠርቶ አላቸው፥ “በየቤታችሁ ጠቦት ምረጡ፤ ወስዳችሁም ለፋሲካ እረዱት። |
ካህናቱና ሌዋውያኑም ሁሉ በሥርዓቱ መሠረት ራሳቸውን አነጹ፤ ሌዋውያኑም በፋሲካው በዓል አከባበር ላይ ከምርኮ ለተመለሱት ሕዝብና ለካህናቱ፥ እንዲሁም ለራሳቸው የቀረቡትን እንስሶች ዐረዱ።
ለጒዞ እንደ ተዘጋጀ ሰው ሆናችሁ ወገባችሁን በመታጠቅ ጫማችሁን አድርጋችሁ፥ በትራችሁን በእጃችሁ ይዛችሁ በችኰላ ብሉት፤ እርሱም እኔን እግዚአብሔርን የምታከብሩበት የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤል ሕዝብ አለቆች፥ ጥቂቶቹን ውሰድ፤ ከሕዝቡም ቀድመህ ወደ ፊት ሂድ፤ የዐባይን ወንዝ የመታህበትንም በትር በእጅህ ያዝ፤
እንግዲህ ሂድና የእስራኤልን ሕዝብ አለቆች ሁሉ በአንድነት ሰብስብ፤ የቀድሞ አባቶቻቸው የአብርሃም የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እኔ እግዚአብሔር የተገለጥኩልህ መሆኔንም ንገራቸው፤ ወደ እነርሱ ወርጄ ግብጻውያን በእነርሱ ላይ ያደረሱባቸውን ግፍና ጭቈና መመልከቴን ንገራቸው።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለሕዝብ አመራር በመስጠት የታወቁ ሰባ ሽማግሌዎችን ምረጥ፤ እነርሱንም ሰብስበህ ወደ መገናኛው ድንኳን አምጣቸውና በአጠገብህ ይቁሙ፤
ሁሉም አንድ ዐይነት መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ የጠጡትም ይከተላቸው ከነበረው ከዚያ ከመንፈሳዊ አለት የመነጨ ነበር፤ ያም አለት ራሱ ክርስቶስ ነበር።
የበኲር ልጆችን ለመግደል የታዘዘው መልአክ የእስራኤላውያንን የበኲር ልጆች እንዳይገድል በማለት ሙሴ የፋሲካና የደም መርጨትን ሥርዓት ያደረገው በእምነት ነው።