እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ሰባት ቀን ሙሉ እርሾ ያልነካውና ፈጽሞ ያልቦካ ቂጣ ብቻ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን እርሾውን ሁሉ ከየቤታችሁ ታስወግዳላችሁ፤ ማንም ሰው በነዚያ ሰባት ቀኖች እርሾ ያለበትን እንጀራ ቢበላ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ይወገዳል።
ዘፀአት 12:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ ሰባት ቀን ምንም እርሾ በቤታችሁ መገኘት የለበትም፤ የአገር ተወላጅም ሆነ ወይም መጻተኛ ማንኛውም ሰው የቦካ እንጀራ ቢበላ፥ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ይወገዳል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሰባት ቀን እርሾ በቤታችሁ አይኑር፤ መጻተኛም ሆነ የአገር ተወላጅ እርሾ ያለበትን ቂጣ የበላ ከእስራኤል ማኅበር ይወገድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባት ቀን በቤታችሁ እርሾ አይገኝ፤ እርሾ ያለበትንም እንጀራ የሚበላ ነፍስ፥ ከመጻተኛው ጀምሮ እስከ አገሩ ተወላጅ ድረስ፥ ከእስራኤል ማኅበር ተለይቶ ይወገድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባት ቀን በቤታችሁ እርሾ አይገኝ፤ እርሾ ያለበትንም እንጀራ የሚበላ ሁሉ ያ ሰው ከመጻተኛው ጀምሮ እስከ ሀገር ልጁ ድረስ፥ ከእስራኤል ማኅበር ተለይቶ ይጥፋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባት ቀን በቤታችሁ እርሾ አይገኝ፤ እርሾ ያለበትንም እንጀራ የሚበላ ነፍስ፥ ከመጻተኛው ጀምሮ እስከ አገር ልጁ ድረስ፥ ከእስራኤል ማኅበር ተለይቶ ይጥፋ። |
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ሰባት ቀን ሙሉ እርሾ ያልነካውና ፈጽሞ ያልቦካ ቂጣ ብቻ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን እርሾውን ሁሉ ከየቤታችሁ ታስወግዳላችሁ፤ ማንም ሰው በነዚያ ሰባት ቀኖች እርሾ ያለበትን እንጀራ ቢበላ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ይወገዳል።
እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “የፋሲካ በዓል አከባበር ሥርዓት ይህ ነው፤ ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው የፋሲካን ራት አይብላ፤
ነገር ግን ያልተገረዘ ማንም ሰው አይብላ፤ የውጪ አገር ሰው በመካከላችሁ ቢኖርና የእግዚአብሔርን የፋሲካ በዓል ማክበር ቢፈልግ፥ አስቀድማችሁ በቤተሰቡ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ግረዙ፤ ከዚያም በኋላ የሀገር ተወላጅ እስራኤላዊ እንደ ሆነ ተቈጥሮ የፋሲካን በዓል ለማክበር ከእናንተ ጋር ይተባበር።
ሙሴም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “ይህ ቀን በባርነት ስትገዙ የኖራችሁበትን የግብጽን ምድር ለቃችሁ የወጣችሁበት ስለ ሆነ ይህን ቀን አስታውሱ፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ በመታደግ ያወጣችሁ በዚህ ቀን ነው፤ ስለዚህ በዚህ ቀን እርሾ የነካው እንጀራ አትብሉ።
ከግብጽ በወጣችሁበት በአቢብ ወር፥ እኔ ባዘዝኳችሁ አኳኋን የቂጣን በዓል አክብሩ፤ ይህ በዓል በሚከበርባቸው በሰባቱ ቀኖች ውስጥ እርሾ የነካው እንጀራ አትብሉ፤ ለእኔ ልትሰግዱ በምትመጡበት ጊዜ መባ ሳትይዙ አትምጡ።
“ከግብጽ የወጣችሁት በአቢብ ወር ስለ ሆነ የቂጣን በዓል በመጠበቅ በየዓመቱ አክብሩ፤ እንዳዘዝኳችሁ በአቢብ ወር እስከ ሰባት ቀን ቂጣ ብሉ።
ንጹሕ የሆነ እና ወደ ሩቅ አገር ያልሄደ ማንኛውም ሰው የፋሲካን በዓል በወቅቱ ባያከብር ከሕዝቤ ይለይ፤ መባውን በተወሰነው ጊዜ ባለማቅረቡ፥ ስለ ኃጢአቱ ተገቢውን ቅጣት ይቀበላል።
ያንንም ራት በምትመገብበት ጊዜ እርሾ የነካው እንጀራ አትብላ፤ በዚያ ዐይነት አስቸኳይ ሁኔታ ግብጽን ለቀህ በወጣህበት ጊዜ እንዳደረግኸው ሰባት ቀን ሙሉ እርሾ ያልነካው ቂጣ ትበላለህ፤ ይህን ቂጣ ብላ፤ እርሱም የሥቃይ እንጀራ ተብሎ ይጠራል፤ ይኸውም በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ብዙ ሥቃይ ከተቀበልክበት ከግብጽ ምድር የወጣህበትን ቀን ታስታውሳለህ።