አስቴር 3:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተ መንግሥት ሥራ ላይ የተመደቡ ሌሎች ባለሥልጣኖች መርዶክዮስን “የንጉሡን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋለህ?” እያሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ በንጉሡ በር ያሉት የንጉሡ አገልጋዮች መርዶክዮስን፣ “የንጉሡን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋለህ?” ሲሉ ጠየቁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በንጉሡም በር ያሉት የንጉሡ ባሪያዎች መርዶክዮስን፦ የንጉሡን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋለህ? አሉት። |
ንጉሡም በግዛቱ ሥር ያሉ ባለሥልጣኖች ሁሉ በጒልበታቸው ተንበርክከው እየሰገዱ እጅ በመንሣት ያከብሩት ዘንድ አዘዘ፤ እነርሱም ሁሉ እንደ ታዘዙት አደረጉ፤ ይህን ለማድረግ እምቢ ያለ መርዶክዮስ ብቻ ነበር።
ከቀን ወደ ቀን ሐሳቡን ለማስቀየር ይጥሩ ነበር፤ እርሱ ግን ሊሰማቸው አልወደደም፤ እንዲያውም እኔ አይሁዳዊ ስለ ሆንኩ ለሃማን መስገድ አይገባኝም በማለት ቊርጥ ውሳኔውን ገለጠላቸው ከዚህ በኋላ የመርዶክዮስን ትዕቢት እንዴት መታገሥ ይቻላል? እያሉ በመገረም ጉዳዩን ለሃማን ነገሩት።