መክብብ 10:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕውቀት የጐደለው ሞኝ ሰው ወደ ከተማ መውጣት ስለሚሳነው በሥራው ይደክማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞኝ ሥራ ራሱን ያደክመዋል፤ ወደ ከተማ የሚወስደውንም መንገድ አያውቅም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰነፍ ሥራ ያደክመዋል ወደ ከተማ መሄድ አያውቅምና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰነፍ ድካሙ ያሠቃየዋል፥ ወደ ከተማ መሄድን አያውቅምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰነፍ ሥራ ያደክመዋል ወደ ከተማ መሄድ አያውቅምና። |
ለማይጠቅም ምግብ ገንዘባችሁን ለምን ታወጣላችሁ? ለማያጠግብ ነገር ጒልበታችሁን ለምን ታባክናላችሁ? አሁንም በጥንቃቄ አድምጡኝና መልካም የሆነውን ምግብ ብሉ፤ በምርጥ ምግብም ራሳችሁን አስደስቱ።
ጻድቃን ሲሞቱ ማንም ትኲረት አይሰጠውም፤ ደጋግ ሰዎች በሞት ሲወሰዱ ከክፉ ነገር እንዲድኑ የተወሰዱ መሆናቸውን ማንም ሰው ሊያስተውለው አይችልም።
ሰው ሁሉ እንደነዚህ ባሉት ሰዎች ላይ በመሳለቂያ እንቆቅልሽ እንዲህ ይላል፦ “ያንተ ያልሆነውን የምታግበሰብስ ወዮልህ! በመያዣነት በተወሰዱ ዕቃ ራስህን የምታበለጽገው እስከ መቼ ነው?”