ከጥንት ጀምሮ ጸንተው ከሚኖሩት ተራራዎችና ዘለዓለማውያን ከሆኑት ኮረብታዎችም ከሚገኘው ደስ ከሚያሰኝ በረከት ሁሉ የአባትህ በረከት ይበልጣል። እንግዲህ ይህ ሁሉ በረከት በዮሴፍ ራስ ላይ ይሁን፤ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም በዮሴፍ አናት ላይ ይውረድ።
ዘዳግም 33:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ከጥንት የነበሩ ተራሮቻቸውና ከኮረብቶቻቸው በተትረፈረፈ ምርጥ ምርት የበለጸጉ ይሁኑ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጥንት ተራሮች በተገኘ ምርጥ ስጦታ፣ በዘላለማዊ ኰረብቶች ፍሬያማነት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከቀደሙትም ከጥንት ተራሮች ከፍተኛነት፥ በዘለዓለሙም ኮረብቶች ገናንነት፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቀደሙትም ተራሮች ከፍተኛነት፥ ከዘለዓለሙ ኮረብቶች ራሶች፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቀደሙትም ተራሮች ከፍተኛነት፥ 2 በዘላለሙም ኮረብቶች ገናንነት፥ |
ከጥንት ጀምሮ ጸንተው ከሚኖሩት ተራራዎችና ዘለዓለማውያን ከሆኑት ኮረብታዎችም ከሚገኘው ደስ ከሚያሰኝ በረከት ሁሉ የአባትህ በረከት ይበልጣል። እንግዲህ ይህ ሁሉ በረከት በዮሴፍ ራስ ላይ ይሁን፤ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም በዮሴፍ አናት ላይ ይውረድ።
እርሱ ሲቆም ምድር ትናወጣለች፤ እርሱ ሲመለከታቸው ሕዝቦች ይንቀጠቀጣሉ፤ የጥንቱ ተራራዎች ይናዳሉ፤ ከጥንት ጀምሮ የእርሱ መረማመጃ የነበሩት ኰረብቶች ወደ ታች ይሰጥማሉ።
ወንድሞች ሆይ! እንግዲህ ጌታ እስኪመጣ ድረስ በትዕግሥት ጠብቁ፤ ገበሬ መሬቱ የመጀመሪያውንና የኋለኛውን ዝናብ እስከሚያገኝ እየታገሠ ክቡር ዋጋ ያለውን የመሬቱን ፍሬ ይጠባበቃል።