ስለዚህም ንጉሥ ሴዴቅያስ በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ እንዲዘጋብኝ አዘዘ፤ እኔም በዚያ ቈየሁ፤ ዳቦ ከከተማይቱ ጨርሶ እስከ ጠፋም ድረስ ከዳቦ መጋገሪያዎች አንድ ዳቦ በየቀኑ ይሰጠኝ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 28:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጳውሎስ በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ተቀመጠ፤ ወደ እርሱ የሚመጡትንም ሰዎች ሁሉ ይቀበል ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጳውሎስም ራሱ በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ተቀመጠ፤ ወደ እርሱ የሚመጡትንም ሁሉ በደስታ ይቀበል ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጳውሎስም በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ተቀመጠ፤ ወደ እርሱም የሚመጡትን ሁሉ ይቀበል ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጳውሎስም በገንዘቡ በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ተቀመጠ፤ ወደ እርሱ የሚመጣውንም ሁሉ ይቀበል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጳውሎስም በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ተቀመጠ፥ ወደ እርሱም የሚመጡትን ሁሉ ይቀበል ነበር፤ |
ስለዚህም ንጉሥ ሴዴቅያስ በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ እንዲዘጋብኝ አዘዘ፤ እኔም በዚያ ቈየሁ፤ ዳቦ ከከተማይቱ ጨርሶ እስከ ጠፋም ድረስ ከዳቦ መጋገሪያዎች አንድ ዳቦ በየቀኑ ይሰጠኝ ነበር።
እርሱም “ኑና እዩ” አላቸው። ስለዚህ ሄዱና የት እንደሚኖር አዩ። በዚያን ቀን ከእርሱ ጋር አብረው ዋሉ፤ ጊዜው ወደ ዐሥር ሰዓት ገደማ ነበር።
ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በመንፈሱ አስቦ “እዚያ ከደረስኩ በኋላ ወደ ሮም መሄድ አለብኝ” አለ።
እነርሱ የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸውን? እኔ ከእነርሱ ይበልጥ የክርስቶስ አገልጋይ ነኝ፤ ይህንንም ስል እንደ እብድ ሆኜ ነው የምናገረው፤ ከእነርሱ ይበልጥ ብዙ ጊዜ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ታስሬአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ተገርፌአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ለሞት አደጋ ደርሼአለሁ፤