ሐዋርያት ሥራ 28:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተናገረውም ቃል ይህ ነው፦ ‘ወደዚህ ሕዝብ ሂድና መስማትስ ትሰማላችሁ፤ ግን አታስተውሉም፤ ማየትስ ታያላችሁ፤ ግን ልብ አታደርጉም በላቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ወደዚህ ሕዝብ ሂድ፤ እንዲህም በላቸው፤ “መስማትን ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትን ታያላችሁ፤ ነገር ግን አትመለከቱም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደዚህ ሕዝብ ሂድና፥ መስማትን ትሰማላችሁና አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁና አትመለከቱም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘ወደዚህ ሕዝብ ሂድና እንዲህ በላቸው፦ መስማትን ትሰማላችሁ፤ ግን አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁ፤ ግን አትመለከቱም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ‘ወደዚህ ሕዝብ ሂድና፦ መስማትን ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትንም ታያላችሁና አትመለከቱም፤ |
አስደናቂ ተአምርን አከታትዬ በማምጣት ይህ ሕዝብ እንዲገረም አደርገዋለሁ፤ የጥበበኞች ጥበብ ትሰወራለች፤ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትረሳለች።”
ስጠራ ማንም ስላልመለሰልኝ፥ ስናገር ማንም ስላላዳመጠኝ ነገር በፊቴ ክፉ የሆነውን ነገር ስላደረጉና የማያስደስተኝን ስለ መረጡ እኔም በእነርሱ ላይ ቅጣት አመጣባቸዋለሁ።”
“የሰው ልጅ ሆይ! አንተ የምትኖረው ዐመፀኞች በሆኑ ሕዝብ መካከል ነው፤ እነርሱ ዐመፀኞች ከመሆናቸው የተነሣ ዐይን እያላቸው አያዩም፤ ጆሮም እያላቸው አይሰሙም።
ይህም የሚሆነው፥ ‘እነርሱ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ኃጢአታቸው ይቅር እንዳይባልላቸው፥ ማየትን እያዩ ልብ አያደርጉም፤ መስማትን እየሰሙ አያስተውሉም፤’ ” በተባለው መሠረት ነው።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ሌሎች ግን ሁሉ ነገር በምሳሌ ይነገራቸዋል፤ እነርሱ እያዩ ልብ እንዳያደርጉ፥ እየሰሙም እንዳያስተውሉ ነው።”
እነርሱም እርስ በርሳቸው ሳይስማሙ ተለያዩ። ሆኖም ከመለያየታቸው በፊት ጳውሎስ ለመጨረሻ ጊዜ ሲናገር እንዲህ አለ፦ “መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ አማካይነት ለአባቶቻችሁ የተናገረው ልክ ነበር!
እግዚአብሔር ግን እስከ ዛሬይቱ ዕለት ድረስ ያለፋችሁበትን ሁኔታ የምታዩበት ዐይን፥ የምትሰሙበት ጆሮ፥ የምታስተውሉበት አእምሮ አልሰጣችሁም።