ሐዋርያት ሥራ 28:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እርስ በርሳቸው ሳይስማሙ ተለያዩ። ሆኖም ከመለያየታቸው በፊት ጳውሎስ ለመጨረሻ ጊዜ ሲናገር እንዲህ አለ፦ “መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ አማካይነት ለአባቶቻችሁ የተናገረው ልክ ነበር! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርስ በርሳቸውም አልተስማሙም፤ ጳውሎስም እንዲህ የሚል የመጨረሻ ቃል ከተናገራቸው በኋላ ሄዱ፤ “መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ አማካይነት ለአባቶቻችሁ በትክክል እንዲህ ብሎ ተናግሯል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርስ በርሳቸውም ባልተስማሙ ጊዜ፥ ጳውሎስ አንዲት ቃል ከተናገረ በኋላ ሄዱ፤ እንዲህም አለ፦ መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ ለአባቶቻችን የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስ በርሳቸውም ባልተስማሙ ጊዜ ጳውሎስ አንዲት ቃል ከተናገረ በኋላ ከእርሱ ተመለሱ፤ እንዲህም አላቸው፥ “መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ አንደበት ለአባቶቻችን በእውነት እንዲህ ብሎ መልካም ነገር ተናግሮአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስ በርሳቸውም ባልተስማሙ ጊዜ፥ ጳውሎስ አንዲት ቃል ከተናገረ በኋላ ሄዱ፤ እንዲህም አለ፦ “መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ ለአባቶቻችን፦ |
እርሱ ግን እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እናንተ ግብዞች! ኢሳይያስ ስለ እናንተ፥ ‘ይህ ሕዝብ በአፉ ብቻ ያከብረኛል እንጂ ልቡ ከእኔ የራቀ ነው!
የተናገረውም ቃል ይህ ነው፦ ‘ወደዚህ ሕዝብ ሂድና መስማትስ ትሰማላችሁ፤ ግን አታስተውሉም፤ ማየትስ ታያላችሁ፤ ግን ልብ አታደርጉም በላቸው፤