“ከየሀገሩ ከስደት ተርፋችሁ የተመለሳችሁ፥ ተሰብስባችሁ በአንድነት ቅረቡ! የእንጨት ጣዖቶችን ይዘው የሚዘዋወሩና ማዳን ወደማይችል ጣዖት የሚጸልዩ ዕውቀት የሌላቸው ናቸው።
ሐዋርያት ሥራ 28:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሦስት ወር በማልታ ከቈየን በኋላ ክረምቱን በደሴቲቱ ባሳለፈው በእስክንድርያው መርከብ ተሳፍረን ተነሣን፤ መርከቡ ዲዮስቆሮስ የተባሉ የመንታ አማልክት አርማ ነበረበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሦስት ወር በኋላም፣ በደሴቲቱ ክረምቱን ቆሞ በሰነበተ በአንድ መርከብ ተነሥተን ጕዞ ጀመርን። ይህም መርከብ የእስክንድርያ ሲሆን፣ በላዩ ላይ የመንታ አማልክቱ የዲዮስቆሮስ አርማ ነበረበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሦስት ወርም በኋላ በደሴቲቱ ከርሞ በነበረው በእስክንድርያው መርከብ ተነሣን፤ በእርሱም የዲዮስቆሮስ ዓላማ ነበረበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሦስት ወር በኋላም በዚያች ደሴት ወደ ከረመችው ወደ እስክንድርያ መርከብ ወጣን፤ በዚያች መርከብ ላይም የዲዮስቆሮስ ምልክት ነበረባት፤ ይኸውም “የመርከበኞች አምላክ” የሚሉት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሦስት ወርም በኋላ በደሴቲቱ ከርሞ በነበረው በእስክንድርያው መርከብ ተነሣን፥ በእርሱም የዲዮስቆሮስ አላማ ነበረበት። |
“ከየሀገሩ ከስደት ተርፋችሁ የተመለሳችሁ፥ ተሰብስባችሁ በአንድነት ቅረቡ! የእንጨት ጣዖቶችን ይዘው የሚዘዋወሩና ማዳን ወደማይችል ጣዖት የሚጸልዩ ዕውቀት የሌላቸው ናቸው።
መርከበኞቹም እጅግ ስለ ፈሩ እያንዳንዱ ወደ አምላኩ ጮኸ፤ የመርከቢቱን ክብደት ለመቀነስ አስበው በውስጥዋ የነበረውን ዕቃ እያወጡ ወደ ባሕር ጣሉ፤ ዮናስ ግን በመርከቢቱ ታችኛ ክፍል ወርዶ በመተኛቱ በከባድ እንቅልፍ ላይ ነበር።
በዚያን ጊዜ “የነጻ ወጪዎች ምኵራብ” ከተባለው የአይሁድ ጸሎት ቤት ሰዎች፥ ከቀሬናና ከእስክንድርያ ሰዎች፥ ከኪልቅያና ከእስያ አንዳንድ ሰዎች ተነሥተው እስጢፋኖስን በመቃወም ይከራከሩት ነበር።
ስለዚህ ለጣዖት የተሠዋውን ሥጋ ስለ መብላት የሆነ እንደ ሆነ ጣዖት ሕይወት የሌለው እንደ ሆነና ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።