ቀድሞ ያልተነገራቸውን ነገር ስለሚያዩና ያልሰሙትን ነገር ስለሚያስተውሉ ብዙ ሕዝቦች ስለ አገልጋዬ ይደነቃሉ፤ ነገሥታትም በእርሱ በመደነቅ የሚናገሩትን ያጣሉ።”
ሐዋርያት ሥራ 25:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አግሪጳም ፊስጦስን “እኔም ይህ ሰው ሲናገር መስማት እፈልጋለሁ” አለው። ፊስጦስም “ነገ ትሰማዋለህ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አግሪጳም ፊስጦስን፣ “እኔም እኮ ይህ ሰው ሲናገር መስማት እፈልግ ነበር” አለው። እርሱም፣ “እንግዲያውስ ነገ ትሰማዋለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አግሪጳም ፊስጦስን “ያንንስ ሰው እኔ ዳግም እኮ እሰማው ዘንድ እወድ ነበር፤” አለው። እርሱም “ነገ ትሰማዋለህ፤” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አግሪጳም ፊስጦስን፥ “እኔም ያን ሰው ልሰማው እወዳለሁ” አለው፤ ፊስጦስም፥ “እንግዲያስ ነገ ትሰማዋለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አግሪጳም ፊስጦስን፦ “ያንንስ ሰው እኔ ዳግም እኮ እሰማው ዘንድ እወድ ነበር” አለው። እርሱም፦ “ነገ ትሰማዋለህ” አለው። |
ቀድሞ ያልተነገራቸውን ነገር ስለሚያዩና ያልሰሙትን ነገር ስለሚያስተውሉ ብዙ ሕዝቦች ስለ አገልጋዬ ይደነቃሉ፤ ነገሥታትም በእርሱ በመደነቅ የሚናገሩትን ያጣሉ።”
ነገር ግን ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ሰዎች እናንተን ይይዙአችኋል፤ ያሳድዱአችኋል፤ ወደ ምኲራብና ወደ ወህኒ ቤትም አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ስለ ስሜም ወደ ነገሥታትና ወደ ገዥዎች ይወስዱአችኋል።
ጌታም ሐናንያን እንዲህ አለው፦ “እርሱ ስሜን ለአረማውያን፥ ለነገሥታትና ለእስራኤል ሰዎች የሚያሳውቅ፥ የእኔ ምርጥ መሣሪያ ስለ ሆነ ወደ እርሱ ሂድ፤