ዮናዳብም እንዲህ አለው፤ “ይህ ከሆነ እንግዲህ የታመምህ መስለህ አልጋህ ላይ ተኛ፤ አባትህ ሊጠይቅህ ሲመጣ፥ ‘እኅቴ ትዕማርን መጥታ እንድታስታምመኝ እባክህ ንገራት፤ እዚህ በአጠገቤ እያየኋት ምግብ አዘጋጅታ እርስዋ ራስዋ እንድታጐርሰኝ እፈልጋለሁ’ በለው።”
ሐዋርያት ሥራ 23:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እናንተ ከሸንጎው ጋር ተስማምታችሁ በጥብቅ የምትመረምሩት ነገር እንዳለ በማስመሰል ጳውሎስን እንዲያመጡላችሁ አዛዡን ጠይቁት፤ እኛም እዚህ ከመድረሱ በፊት ልንገድለው ተዘጋጅተናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ እናንተ ከሸንጎው ጋራ ሆናችሁ፣ ስለ ጕዳዩ ትክክለኛ የሆነ ተጨማሪ መረጃ ከርሱ እንደምትፈልጉ አስመስላችሁ ጳውሎስን ወደ እናንተ እንዲሰድደው የጦር አዛዡን ለምኑት፤ እኛም ገና ወደዚህ ሳይደርስ ልንገድለው ዝግጁ ነን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ አሁን እናንተ ከሸንጎው ጋር ሆናችሁ ስለ እርሱ አጥብቃችሁ እንደምትመረምሩ መስላችሁ ወደ እናንተ እንዲያወርደው ለሻለቃው አመልክቱት፤ እኛም ሳይቀርብ እንድንገድለው የተዘጋጀን ነን፤” አሉአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እናንተ ከሸንጎው ጋር ወደ ሻለቃው ሂዱና የምትመረምሩትና የምትጠይቁት አስመስላችሁ ጳውሎስን እንዲያመጣው ንገሩት፤ እኛ ግን ወደ እናንተ ከመድረሱ አስቀድሞ ልንገድለው ቈርጠናል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ አሁን እናንተ ከሸንጎው ጋር ሆናችሁ ስለ እርሱ አጥብቃችሁ እንደምትመረምሩ መስላችሁ ወደ እናንተ እንዲያወርደው ለሻለቃው አመልክቱት፤ እኛም ሳይቀርብ እንድንገድለው የተዘጋጀን ነን አሉአቸው። |
ዮናዳብም እንዲህ አለው፤ “ይህ ከሆነ እንግዲህ የታመምህ መስለህ አልጋህ ላይ ተኛ፤ አባትህ ሊጠይቅህ ሲመጣ፥ ‘እኅቴ ትዕማርን መጥታ እንድታስታምመኝ እባክህ ንገራት፤ እዚህ በአጠገቤ እያየኋት ምግብ አዘጋጅታ እርስዋ ራስዋ እንድታጐርሰኝ እፈልጋለሁ’ በለው።”
እነርሱ ወደ ክፉ ሥራ ይሮጣሉ፤ ንጹሕ ደምንም ለማፍሰስ ይቸኲላሉ፤ ሐሳባቸው የበደል ሐሳብ ነው፤ በሚያልፉበት ቦታ ሁሉ ማጥፋትና ማፈራረስ ልማዳቸው ነው፤
በማግስቱ አዛዡ፥ አይሁድ ጳውሎስን የከሰሱበት ትክክለኛ ምክንያት ምን እንደ ሆነ ለማወቅ ፈለገ፤ ስለዚህ የካህናት አለቆችና የሸንጎው አባሎች በሙሉ እንዲሰበሰቡ አዘዘ፤ ጳውሎስንም ከእስራቱ ፈቶ ወሰደና በፊታቸው አቀረበው።
ጳውሎስም ሸንጎውን ትኲር ብሎ ተመለከተና “ወንድሞቼ ሆይ! እስከ ዛሬ ድረስ ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ፊት የኖርኩት በመልካም ኅሊና ነው” አለ።
ጳውሎስ እዚያ ከነበሩት ሰዎች እኩሌቶቹ ሰዱቃውያን እኩሌቶቹ ደግሞ ፈሪሳውያን መሆናቸውን ዐውቆ “ወንድሞቼ ሆይ! እኔ ከፈሪሳዊ የተወለድኩ ፈሪሳዊ ነኝ፤ እነሆ! አሁን በፍርድ ፊት የቀረብኩት በተሰጠው ተስፋና በሙታን ትንሣኤ ምክንያት ነው” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ በሸንጎው መካከል ተናገረ።