ስለዚህም በእርሱ ዘንድ የነበሩትን ባዕዳን አማልክት ሁሉ አምጥተው ለያዕቆብ ሰጡት፤ እንዲሁም በየጆሮአቸው አድርገውት የነበረውን ጒትቻ ሁሉ አውልቀው ሰጡት፤ እርሱም ሁሉንም ወሰደና በሴኬም አጠገብ በነበረው የወርካ ዛፍ ሥር ቀበራቸው።
ሐዋርያት ሥራ 19:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ አስማተኞችም የአስማት መጽሐፎቻቸውን ሰብስበው በሕዝቡ ሁሉ ፊት አቃጠሉአቸው፤ የመጽሐፎቹ ዋጋ ሲተመን ኀምሳ ሺህ ጥሬ ብር ሆኖ ተገኘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሲጠነቍሉ ከነበሩትም መካከል ብዙዎች መጽሐፋቸውን ሰብስበው በማምጣት በሕዝብ ፊት አቃጠሉ፤ ዋጋቸውም ሲሰላ ዐምሳ ሺሕ ብር ያህል ሆኖ ተገኘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአስማተኞችም ብዙዎቹ መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት፤ ዋጋውም ቢታሰብ አምሳ ሺህ ብር ሆኖ ተገኘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙዎች አስማተኞችም መጽሐፎቻቸውን እየሰበሰቡ እያመጡ በሕዝቡ ሁሉ ፊት በእሳት ያቃጥሉ ነበር፤ ያቃጠሏቸው የመጽሐፎች ዋጋም አምሳ ሺህ ብር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአስማተኞችም ብዙዎቹ መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት፤ ዋጋውም ቢታሰብ አምሳ ሺህ ብር ሆኖ ተገኘ። |
ስለዚህም በእርሱ ዘንድ የነበሩትን ባዕዳን አማልክት ሁሉ አምጥተው ለያዕቆብ ሰጡት፤ እንዲሁም በየጆሮአቸው አድርገውት የነበረውን ጒትቻ ሁሉ አውልቀው ሰጡት፤ እርሱም ሁሉንም ወሰደና በሴኬም አጠገብ በነበረው የወርካ ዛፍ ሥር ቀበራቸው።
ሳኦል ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ ባለመገኘቱ ምክንያት ሞተ፤ እርሱ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አልፈጸመም፤ እንዲያውም የሙታን መናፍስት ጠሪዎችን በመጠየቅ መመሪያ ለማግኘት ሞከረ እንጂ እግዚአብሔርን አልጠየቀም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ገደለው፤ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አስተላለፈ።
የገዛ ወንዶች ልጆቹንም በሂኖም ሸለቆ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ እርሱም ራሱ ሟርተኛና አስማተኛ ሆኖ፥ ከጠንቋዮችና ከሙታን ጠሪዎች ምክርን ይጠይቅ ነበር፤ በዚህም ሁሉ አድራጎቱ ታላቅ ኃጢአት ስለ ሠራ፥ እግዚአብሔርን አስቈጣ።
ከዚህ በኋላ የንጉሡ አስማተኞች በአስማታቸው እንደዚሁ አደረጉ፤ ንጉሡም ልቡን በማደንደን ጸና፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረውም ንጉሡ ሙሴንና አሮንን ማዳመጥ እምቢ አለ።
“በመንተባተብ የሚቀባጥሩትን ሟርተኞችንና የሙታን መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ” እያሉ የሚሰብኩአችሁ ወገኖች አሉ፤ ታዲያ፥ ስለ ሕያዋን ሙታንን ከመጠየቅ ይልቅ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን?
ስለዚህ ወደ እርሱ መጥተው ያየውን ሕልም ይነግሩት ዘንድ ጠንቋዮች፥ አስማተኞች፥ መተተኞችና የከለዳውያን ኮከብ ቈጣሪዎች እንዲጠሩ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ እነርሱም መጥተው በፊቱ ቆሙ፤
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ዐሥር የብር መሐለቅ ያላት ሴት ከዐሥሩ አንዱ መሐለቅ ቢጠፋባት መብራት አብርታ፥ ቤትዋን ጠርጋ የጠፋባትን መሐለቅ እስክታገኝ ድረስ በጥንቃቄ አትፈልገውምን?
እናንተ የተሻለና ነዋሪ ሀብት በሰማይ እንዳላችሁ በማወቃችሁ ለእስረኞች ራራችሁላቸው፤ ንብረታችሁም ሲወሰድባችሁ ታግሣችሁ ሁኔታውን በደስታ ተቀበላችሁ።