ሐዋርያት ሥራ 15:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነዚህ ከሚከተሉት አስፈላጊ ነገሮች በስተቀር ሌላ ከባድ ሸክም እንዳንጭንባችሁ መንፈስ ቅዱስና እኛ መልካም ሆኖ አግኝተነዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነዚህ አስፈላጊ ነገሮች በቀር ሌላ ተጨማሪ ሸክም እንዳንጭንባችሁ፣ ለመንፈስ ቅዱስም ለእኛም መልካም መስሎ ታይቶናል፤ ይኸውም፦ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥርዐት እንዳናከብድ ሌላም ሸክም እንዳንጨምር መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ነውና፤ ነገር ግን ይህን በግድ ትተዉ ዘንድ እናዝዛችኋለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።” |
የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል። እርሱ የሚናገረው የሰማውን እንጂ የራሱን ስላልሆነ እርሱ ወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ይነግራችኋል።
ስለዚህ በአንድነት ከተሰበሰብን በኋላ መልእክተኞችን መርጠን ከተወደዱት ወንድሞቻችን ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር ወደ እናንተ ልንልካቸው ተስማማን።
ጳውሎስና ሲላስ በየከተማው ሲያልፉ በኢየሩሳሌም ባሉት ሐዋርያትና ሽማግሌዎች የተወሰነውን ደንብ ለአማኞች ያስታውቁ ነበር፤ በሥራ ላይ እንዲያውሉትም ያሳስቡአቸው ነበር።
ስላላገቡ ሰዎች ከጌታ የተቀበልኩት ትእዛዝ የለኝም፤ ነገር ግን በጌታ ምሕረት እምነት የሚጣልብኝ እንደ መሆኔ መጠን የራሴ ሐሳብ ከዚህ ቀጥሎ ያለው ነው፤
እነዚህ ነቢያት ያገለግሉ የነበሩት እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳልነበረ ተገልጦላቸዋል፤ ያገለገሉአችሁም ከሰማይ በተላከው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት አሁን ወንጌልን ያበሠሩአችሁ ሰዎች የነገሩአችሁን በመግለጥ ነው፤ ይህን ነገር መላእክት እንኳ ለማየት ይመኙት ነበር።
“በትያጥሮን ላላችሁትና ይህን መጥፎ ትምህርት ላልተቀበላችሁት ሁሉ፥ እንዲሁም አንዳንዶች ‘የሰይጣን ጥልቅ ምሥጢር ነው’ የሚሉትን ላልተከተላችሁ ሌላ ሸክም አልጭንባችሁም፤