ሐዋርያት ሥራ 14:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም በደረሱ ጊዜ አማኞችን በአንድነት ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ ያደረገውን ሁሉና አሕዛብም እንዲያምኑ እንዴት አድርጎ በር እንደ ከፈተላቸው ነገሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እዚያም በደረሱ ጊዜ፣ ቤተ ክርስቲያንን በአንድነት ሰብስበው፣ እግዚአብሔር በእነርሱ አማካይነት ያደረገውን ሁሉ፣ ደግሞም ለአሕዛብ እንዴት የእምነትን በር እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደረሱም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንጾኪያም በደረሱ ጊዜ ምእመናኑን ሁሉ ሰብስበው እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ሁሉ፥ ለአሕዛብም የሃይማኖትን በር እንደ ከፈተላቸው ነገሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደረሱም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ። |
እነርሱም ይህንን በሰሙ ጊዜ የሚመልሱትን አጥተው ዝም አሉ፤ “እንግዲህ እግዚአብሔር ለአሕዛብም ለአዲስ ሕይወት የሚያበቃቸውን ንስሓ ሰጥቶአቸዋል፤” በማለትም እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
በዚህ ጊዜ ጉባኤው ጸጥ ብሎ በርናባስና ጳውሎስ በእነርሱ አማካይነት እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ያደረገውን ተአምርና ድንቅ ነገር ሁሉ ሲናገሩ በመገረም አዳመጣቸው።
ክርስቲያኖች በሚሰበሰቡበት ጊዜ እያንዳንዱ ክርስቲያን በተለያዩ ቋንቋዎች ቢናገርና የማያውቁ ወይም የማያምኑ ሰዎች ቢመጡ ተናጋሪዎችን “እነዚህ ሰዎች አብደዋል” አይሉምን?
ነገር ግን እኔ አሁን የሆንኩትን ሆኜ የምገኘው በእግዚአብሔር ጸጋ ነው፤ የተሰጠኝም ጸጋ ያለ ፍሬ አልቀረም፤ እንዲያውም ከሌሎቹ ይበልጥ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ነገር ግን ይህን ያደረገው ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።
ከዚህም ጋር እግዚአብሔር ለቃሉ በር እንዲከፍትልንና እኔ በእርሱ ምክንያት ታስሬ የምገኝበትን የክርስቶስን ምሥጢር ማብሠር እንድንችል ለእኛም ጸልዩ።