2 ተሰሎንቄ 3:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ! ደከምን ብላችሁ መልካም ከመሥራት አትቦዝኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ፤ መልካም ሥራን ከመሥራት ከቶ አትታክቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ! መልካም ሥራን ለመሥራት አትታክቱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ! መልካም ሥራን ለመሥራት አትታክቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ መልካም ሥራን ለመሥራት አትታክቱ። |
እነሆ፥ እናንተ እየተሳለቃችሁ ‘ይህ ሁሉ ምን አሰልቺ ነገር ነው!’ ትላላችሁ። የተሰረቀውን፥ አንካሳውን ወይም የታመመውን እንስሳ ለመሥዋዕትነት ታቀርባላችሁ፤ እኔ ይህን የምቀበል ይመስላችኋልን?
ሁሉ ነገር በክርስቶስ ሥልጣን ሥር ከሆነ በኋላ እግዚአብሔር አብ ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ ወልድ ራሱ ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር በአደረገለት በእግዚአብሔር አብ ሥልጣን ሥር ይሆናል።
“የጦር መሪዎች በሌላም በኩል እንዲህ ብለው ይጠይቁ፥ ‘ወኔ የጐደለው ፈሪ ሰው በመካከላችሁ ይገኛልን? እንዲህ ያለ ሰው ወደ ቤቱ ይመለስ፤ እንዲህ ያለ ሰው የሌሎችን ወኔ ያቀዘቅዛል፤’
በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንዴት መኖር እንደሚገባችሁ ከእኛ ተምራችኋል፤ አሁንም የምትኖሩት እንዲሁ ነው፤ በጌታ በኢየሱስ ስም የምንለምናችሁና የምንመክራችሁም ከዚህ በፊት ካደረጋችሁት ይበልጥ እንድታደርጉ ነው።
እግዚአብሔር እንደ ልጆቹ አድርጎ እንዲህ ሲል የመከራችሁን ረስታችኋል፤ “ልጄ ሆይ! የጌታን ተግሣጽ አታቃል፤ በቀጣህም ጊዜ ተስፋ አትቊረጥ፤