2 ተሰሎንቄ 2:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በቃላችንም ሆነ በመልእክታችን ከእኛ የተላለፈላችሁን ትምህርት አጥብቃችሁ ያዙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በአንደበታችንም ሆነ በመልእክታችን ያስተላለፍንላችሁን ትምህርት አጥብቃችሁ ያዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ወንድሞች ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ትውፊት ያዙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲያስ ወንድሞች ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ። |
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ፤ ለጌታ ሥራ የምትደክሙት በከንቱ አለመሆኑን ዐውቃችሁ፥ ሳታቋርጡ ዘወትር የጌታን ሥራ ለመሥራት ትጉ።
በትንቢት ወይም በቃል እንደ ተነገረ ወይም ከእኛ በመልእክት እንደ ተጻፈ አድርጋችሁ “የጌታ ቀን ደርሶአል” በማለት በቶሎ አእምሮአችሁ አይናወጥ፤ አትታወኩም፤
በዚህ መልእክት ያስተላለፍንላችሁን ምክር የማይቀበል ሰው ቢኖር እንዲህ ያለውን ሰው ልብ በሉት፤ እንዲያፍርም ከእርሱ ጋር ግንኙነት አታድርጉ።
ወንድሞች ሆይ! ሥራ ፈት ከሆነውና ከእኛ በተላለፈላችሁ ትውፊት መሠረት ከማይኖር ክርስቲያን ሁሉ እንድትለዩ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።
ወዳጆች ሆይ! ስለ ጋራ መዳናችን ልጽፍላችሁ በብርቱ ፈልጌ ነበር፤ አሁን ግን በማያዳግም ሁኔታ እግዚአብሔር ለሕዝቡ አንድ ጊዜ ስለ ሰጠው እምነት በብርቱ እንድትጋደሉ ለመምከር ልጽፍላችሁ ግድ ሆነብኝ።