ንጉሥ ኪራም በሠለጠኑ መርከበኞች የሚነዱና በራሱ መኰንኖች የሚመሩ መርከቦችን ለሰሎሞን ልኮለት ነበር፤ እነርሱም ከሰሎሞን መኰንኖች ጋር በመሆን ወደ ኦፊር ምድር መጡ፤ ከዚያም ከዐሥራ አምስት ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ ለሰሎሞን ይዘውለት መጡ።
2 ዜና መዋዕል 9:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሰሎሞን በየዓመቱ ኻያ ሦስት ሺህ ኪሎ ያኽል የሚመዝን ወርቅ ያገኝ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሰሎሞን በየዓመቱ የሚገባለት ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት መክሊት የሚመዝን ወርቅ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየዓመቱ ወደ ሰሎሞን የሚመጣው ወርቅ በሚዛን ሲለካ ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት መክሊት ወርቅ ሲሆን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየዓመቱም ወደ ሰሎሞን የሚመጣ የወርቅ ሚዛን ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት መክሊት ወርቅ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነጋድራሶችና ነጋዴዎች ካመጡለት ሌላ በየዓመቱ ወደ ሰሎሞን የሚመጣ የወርቅ ሚዛን ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት መክሊት ወርቅ ነበረ። |
ንጉሥ ኪራም በሠለጠኑ መርከበኞች የሚነዱና በራሱ መኰንኖች የሚመሩ መርከቦችን ለሰሎሞን ልኮለት ነበር፤ እነርሱም ከሰሎሞን መኰንኖች ጋር በመሆን ወደ ኦፊር ምድር መጡ፤ ከዚያም ከዐሥራ አምስት ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ ለሰሎሞን ይዘውለት መጡ።
ንጉሥ ሰሎሞን እርስዋ ካመጣችው ስጦታ በላይ የሳባ ንግሥት የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣት፤ ከዚህ በኋላ ንግሥተ ሳባ ከክብር አጃቢዎችዋ ጋር ወደ አገርዋ ተመልሳ ሄደች።
ንጉሡ ረጅም ዘመን ይኑር! ከሳባ ወርቅ ይምጣለት፤ ስለ እርሱም ዘወትር ጸሎት ይደረግ፤ የእግዚአብሔርም በረከት ዘወትር ከእርሱ ጋር ይሁን!