ዳዊት ሰሎሞንንም እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ የአባትህን አምላክ እንድታውቅ፥ በሙሉ ልብና በፈቃደኛ አእምሮ እንድታገለግለው ዐደራ እልሃለሁ፤ እርሱ ሐሳባችንንና ምኞታችንን ሁሉ ያውቃል፤ ወደ እርሱ ብትቀርብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል፤ ብትተወው ግን እርሱም ለዘለዓለም ይተውሃል፤
2 ዜና መዋዕል 7:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን አንተና ሕዝብህ እኔ የሰጠኋችሁን ሕጎችና ትእዛዞች ባትጠብቁ፥ ባዕዳን አማልክትንም ብታመልኩና፥ ብትሰግዱላቸው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ ግን እኔን ከመከተል ተመልሳችሁ የሰጠኋችሁን ሥርዐቶቼንና ትእዛዞቼን ብትተዉ፣ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታገለግሉና ብታመልኳቸው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እናንተ ግን እኔን ከመከተል ብትመለሱ፥ የሰጠኋችሁንም ሥርዓቴንና ትእዛዜን ብትተዉ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታመልኩ ብትሰግዱላቸውም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እናንተ ግን ብትመለሱ፥ የሰጠኋችሁን ሥርዐቴንና ትእዛዜን ብትተዉ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታመልኩ፥ ብትሰግዱላቸውም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “እናንተ ግን እኔን ከመከተል ብትመለሱ፥ የሰጠኋችሁንም ሥርዓቴንና ትእዛዜን ብትተዉ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታመልኩ ብትሰግዱላቸውም፥ |
ዳዊት ሰሎሞንንም እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ የአባትህን አምላክ እንድታውቅ፥ በሙሉ ልብና በፈቃደኛ አእምሮ እንድታገለግለው ዐደራ እልሃለሁ፤ እርሱ ሐሳባችንንና ምኞታችንን ሁሉ ያውቃል፤ ወደ እርሱ ብትቀርብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል፤ ብትተወው ግን እርሱም ለዘለዓለም ይተውሃል፤
እስራኤላውያን በሙሴ አማካይነት ያዘዝኳቸውን ሕጌን፥ ሥርዓቴንና ድንጋጌዬን ሁሉ በጥንቃቄ ቢጠብቁ ለቀድሞ አባቶቻቸው ከሰጠኋቸው ምድር እንደገና እንዲፈናቀሉ አላደርግም።
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው ሕዝቤ እኔ የሰጠኋቸውን ሕግ በመተዋቸው ነው፤ እነርሱ ለእኔ አልታዘዙም፤ የነገርኳቸውንም ሁሉ አልፈጸሙም።
እናንተ የሮቤልና የጋድ ሰዎች አሁን እግዚአብሔርን ለመከተል እምቢ ብትሉ፥ እርሱም ይህን ሕዝብ እንደገና በምድረ በዳ ይተወዋል፤ በእነርሱም ላይ በሚደርሰው ጥፋት እናንተ ኀላፊዎች ትሆናላችሁ።”
“ነገር ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ባትታዘዝና እኔ ዛሬ የምሰጥህንም ሕጎችና ትእዛዞች በታማኝነት ባትጠብቅ ከዚህ የሚከተለው መርገም ሁሉ ይደርስብሃል፦
በመካከላችሁ ከቀሩት ሕዝቦች ጋር ከቶ አትተባበሩ፤ የአማልክታቸውንም ስም አትጥሩ፤ በእነርሱም አትማሉ፤ ለእነርሱም አገልጋዮች አትሁኑ፤ አትስገዱላቸውም።