2 ዜና መዋዕል 7:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ቤተ መቅደስ እጠብቀዋለሁ፤ በዚህ ቤተ መቅደስ የሚቀርበውንም ጸሎት ሁሉ እሰማለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም በዚህ ስፍራ ወደሚጸለየው ጸሎት ዐይኖቼ ይገለጣሉ፤ ጆሮዎቼም ያደምጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዐይኖቼ ይገለጣሉ፥ ጆሮቼም ያደምጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዐይኖች ይገለጣሉ፤ ጆሮዎችም ያዳምጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዐይኖቼ ይገለጣሉ፤ ጆሮቼም ያደምጣሉ። |
እግዚአብሔር ሆይ! አገልጋዮችህ ስለ ሆኑት የእስራኤል ሕዝብ ደኅንነት ቀንና ሌሊት የማቀርበውን ጸሎቴን ስማ፤ እኔንም አስበኝ፤ እኛ እስራኤላውያን የሠራነውንም ኃጢአት እናዘዛለሁ፤ በእርግጥም እኔና የቀድሞ አባቶቼ በደል ሠርተናል።